Get Mystery Box with random crypto!

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′ #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

የቀጠለ .......

__________
#የዕለተ_ማክሰኞ__ሥነ_ፍጥረታት
ሰሉስ ሰለሰ ሶስት አደረገ ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሆኖ ለፍጥረት ሶስተኛ ቀን ማለት ነው።
የተፈጠሩት ፍጥረታትም 3 ናቸው።
, በጣት የሚለቀሙ አትክልት
, በማጭድ የሚታጨዱ አዝርዕት
, በምሣር የሚቆረጡ ዕፀዋት ናቸው።
(ዘፍ 1፥9-13)
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ይህ ቀን እግዚአብሔር ከአፈር ጋር ተቀላቅሎ የነበረውን ውሃ በምድር ዙርያ ከወሰነው በኋላ ፤ የመሬት ገጽ የታየበት እና ሰማይና ምድር ዛሬ በምናየው ሁኔታ የተዘጋጁት ፤ ምድርም የዛሬ ቅርጿን የያዘችበት ብሩህ ዕለት (ቀን) ነው። እሑድ የተፈጠሩት ፍጥረታት (ሃያውን ዓለማት)  በየቦታቸው የተከናወኑትም በዚሁ ቀን ነው ። ሃያው ዓለማት የሚባሉትም።

-->ዓለማተ መሬት 5 የጋራ ስማቸው ዱዳሌብ

-->ዓለማተ ማይ 4 የጋራ ስማቸው ናጌብ

-->ዓለማተ እሳት 9 የጋራ ስማቸው ኮሬብ

-->ዓለማተ ነፋስ 2  የጋራ ስማቸው አዜብ ናቸው

ገሐነመ እሳት፣ ሲኦል እና ገነት፣ ብሔረ ህያዋን፣ ብሔረ ብፁዓን ተብለው የተሰየሙት በዚህ ቀን ነው።
እግዚአብሔር አስቀድሞ እነዚህን ዓለማት በየቦታቸው ካዘጋጀ በኋላ በመሬት ላይ ሶስት ፍጥረታትን ብቻ ፈጥሯል።

እነዚህም፦
በእጅ የሚለቀሙ:--አትክልት (በመሬት ውስጥ የሚያፈሩ እንደ ካሮት ድንች …)

በማጭድ የሚታጨዱ:--አዝርዕት (የአገዳ እህሎች እንደ ገብስ ስንዴ በቆሎ ጤፍ …)

በመጥረቢያ የሚቆረጡ:--ዕፀዋት (የዛፍ ዓይነቶች እንደ ዋርካ ወይራ ሾላ…) የመሳሰሉት ናቸው።

የተፈጠሩትም ከአራቱ ባህርያት ነው።
ከመሬት እንደ መፈጠራቸው ሲጣሉ አፈር ይሆናሉ።

ከውሃ እንደ መፈጠራቸው በውስጣቸው ፈሳሽ አላቸው።

ከእሳት እንደመፈጠራቸው ይቃጠላሉ።

ከነፋስ እንደመፈጠራቸው አየር (ነፋስ) ያስገባሉ ያስወጣሉ።

ከአራቱ ባህርያት አንዱ ከተጓደለ ግን ይደርቃሉ እነዚህም የምድር ጌጦች ሲሆኑ ሰውም ለምግቡም ሆነ ለሚፈልገው አገልግሎት ይጠቀምባቸዋል።
~~~~~~~~

ቀጣይ ትምህርታችን
ሕያው አለማት
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan


❸❻