Get Mystery Box with random crypto!

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′ ከባለፈው የቀጠለ...... #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱ | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

′ 2ኛ ኮርስ - ነገረ ሃይማኖት ′

ከባለፈው የቀጠለ......
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

__
#ኤረር
በአስራ አ
ንደኛው ሰዓት ለሊት በኤረር ያለትን/የቀሩትን መላእክት ልክ እንደ ራማ በነገድ 30 በአለቃ 3 አድርጎ አስፈሮአቸዋል።

ሀ, በመጀመሪያው ከተማ 10ን ነገድ መኳንንት (መዝ 3፥24 እስከ 6፥10) በማለት ሰዳክያል የተባለውን መላእክ አለቃ አድርጎላቸው አስፍሮአቸዋል።
የስላሴ ቀስተኞች ናቸው። ማቴ 24፥31

ተራራ የሚንድ ድንጋይ የሚሰነጥቅ የእሳት ፍላፃ የእሳት ቀስት ይዘው ሰውን ሁሉ ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ የሚጠብቁ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በትንሣኤ ዘጉባኤ የሰውን ሁሉ አጥንት የሚሰበስቡና ምድርን ለምጽአት እንዲያዘጋጁ የሚላኩ ናቸው፡፡

ለ, በኤረር በሁለተኛው ከተማ አስሩን ነገድ ሊቃናት በማለ አለቃቸው ይሆን ዘንድ ሰላታኤል የተባለውን መላእክ ሾሞታል።
የስላሴ የፈረስ ባልደራስ ናቸው። በልባቸው የሚሳቡትን፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩትን፣ በክንፋቸው የሚበሩትን የሚጠብቁ መላእክት ናቸው።

ሐ, በኤረር በ3ተኛው ከተማ አሥሩን ነገድ መላክት (1ጴጥ 3፥12) ብሎ ሰይሟቸዋል። አለቃቸውም አናንያ ይባላል።
አገልግሎታቸው እንደብረት የፀና የሳት ነጎድጓድን ወደ ምድር የሚወነጭፉ ፀሀይን፣ ጨረቃን፣ ክዋክብትን፣ አዝዕርትን፣ አትክልትን፣ እፅዋትን በላይ በሰማይ በታች በምድር የተፈጠሩትን ሁሉ የሚጠብቁ መላኢክት ናቸው።

እነዚህ መለእክት አርአያቸው/መጠናቸው የተለያየ ነው። ቁመታቸው አምድር እስከ ሰማይ የሚደርሱ መላእክት አሉ። መዝ 84፥3 ዘፍ 38...
በክንፋቸው አንድ ሀገርን የሚያለብሱ መላእክት አሉ። እራሳቸው ተራራ የሚያክል አሉ። መብረቅ ተጎናፅፈው/ለብሰው የሚኖሩ መላእክትም አሉ። በሀሩን ምንጩን በክንፋቸው የሚያቃጥሉ መላኢክት አሉ ማቴ 28፥3 ዮሐ 12፥7

#ብርሀን
እግዚአብሔር እሑድ ጧት ከቀኑ በመጀመሪያው ሰዓት ብርሀን ይሁን ብሎ ቢያዝ በምስራቅ በኩል ብርሀን ተፈጠረ ዘፍ 1፥3-14
ያንንም ብርሀን በምስራቅ በኩል መንገድ ሰራለት። ስሙንም መዕልት አለው። ማዕልትም ማለት ብርሐን ማለት ነው።

#ጨለማ
ከፍጥረት ሁሉ ጥቁር ጥቁሩን ወስዶ በርባኖስን ፈጠራት ይህች በርባኖስም እልፍ አእላፍ ፀሀይ ቢገባባት አትበራም አትታይም ጨለማም ከበርባኖስ ፈጥሮአል።

ስለምን ጨለማን ፈጠረ ቢሉ ጨለማ አይታይም አይዳሰስም እንዲሁም ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርየ መለኮቱ አይመረመርም፣ አይተረጎምም፣ አይዳበስም፣ አይጨበጥም (ዮሐ 1፥18 ፤ መዝ 17፥11-16
~~~~

ቀጣይ_ትምህርታችን
የሰኞ ሥነ-ፍጥረታት
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግልወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
@mahiberekidusan
❸❹