Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለሰማእቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

እንኳን ለሰማእቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሰን፡፡
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የአለምን ክብር በመናቅ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን የታገሰ ስለእግዚአብሔር ሊመሰክር ደሙን ያፈሰሰ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ በከሀድያን ነገስታት ፊት ስለ እግዚአብሔር ለሰባት አመታት የተጋደለ ሶስት ጊዜ ሞቶ የተነሳ ባለገድል ሰማዕት ነው፡፡
በመጨረሻ ዘመኑም ሰማዕትነት ሲቀበል ወደእግዚአብሔር ጸልዮ ሰባውን ነገስታት አስፈጅቷቸዋል፡፡
በዚህም እምነቱ እግዚአብሔር ሰባት አክሊላትን አቀዳጅቶታል፡፡
በስሙ መልካም ስለሚያደርጉት ሁሉ ቃል ኪዳን ተሰጥቶታል፡፡ ብላቴናዋን ከዘንዶ ያዳናት እኛንም ከሚሠነዘርብን መቅሰፍት ከገሃነም በቃል ኪዳኑ ያድነን፡፡
የፈጣኑ ጊዮርጊስ በረከት ረድኤት ይደርብን፡፡ በጸሎቱ ከመጣው እና ከሚመጣው መቅሰፍት ይሰውረን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላድቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡

@mahiberekidusan