Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን። #ሰላም- ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እን | ማኅበረ ቅዱሳን (Mahibere Kidusan)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።

#ሰላም- ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደምን ናችሁ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ከምትጾማቸው አጽዋማት ውስጥ አንዱ ለሆነው ለጾመ ሐዋርያት ወይም ለሰኔ ጾም በሰላም አደረሳችሁ፡፡
"እስመ ጾም እማ ለጸሎት" ጾም የጸሎት እናት ነች፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ጾመዋል። በመጾማቸውም የእግዚአብሔር በረከት በላያቸው አድሮባቸው እስከመጨረሻው ዳርቻ ጸንተው የሰማዕትነትን ጽዋ በመቀበል የጽድቅ አክሊል ተቀዳጅተዋል ።
ጾም በረከተ ስጋን በማሰጠት የነፍስን ቁስል የምትፈውስ ሐኪም ነች፡፡ ጾም አጋንንትን የምንዋጋባት መንፈሳዊ ትጥቅ ነች፡፡ በአጠቃላይ ስለ ጾም እናውራ ብንል ወንዞች ቀለም ዕጽዋቶች ብዕር ቢሆኑ ተጽፎ አይዘልቅም፡፡

የጾም ጥቅም
1.የነፍስ ቁስልን ለመፈወስ
2.ከአጋንንት ቁራኝነት ለመላቀቅ
3.የስጋ ፍላጎትን ለመቀነስ
4.ግብረ እንስሳዊነትን ለመከላከል
5.የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ.......,..

በብሉይ ኪዳን በቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን በሐድስ ኪዳንከ ጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ በመጾም ተዓምቶች በጾም በጸሎት እንደተደረጉ እናት ቤተ ክርስቲያን አስተምራናለች፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም ይህንን የጀመርነውን ጸም ጾመው አልፈዋል ፡፡ ጾመውም መንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸዋል ፡፡ ስለዚህ እኛም ብንጾም በረከተ ስጋ ድህነተ ነፍስ እናገኛለን፡፡
አምላካችን ጾሙን የኃጢአት መደምሰሻ ፣የድያብሎስ ድል መንሻ ፣የመንግስተ ሰማያት መውረሻ ፣የልቦና ማደሻ ያድርግልን፡፡ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@mahiberekidusan