«ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል? እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።" 1ኛ ዮሐ. 4 ፥ 20-21 የሰው ልጅ የተፈጠረበት አራቱ ባሕርያተ ሥጋ ምሳሌነታቸው እንደምንድን ነው ቢሉ፦ # እሳት ፡- በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ይመሰላል። ለምን ቢሉ እሳት ፈቃድ ፈጻሚ ነው አንድ ቦታ ላይ ብንጭረው ሃገርን ሊያወድም ይችላል እግዚአብሔርም ሁሉን ማድረግ የሚችል ምንም ማይሳነው አምላክ መሆኑን። # ውሃ ፡- በእግዚአብሔር ርህራሄ ይመሰላል። ውሃ እድፍን እንደሚያጠራ በኃጥያታችን ተጸጽተን ንስሐ ብንገባ ይቅር ሊለን፣ ከኃጢአታችን ሊያነጻን የታመነ መሆኑን። # ንፋስ፡- በእግዚአብሔር ፈራጅነት ይመሰላል። ንፋስ ገለባውን ከስንዴ እንደሚለይ እግዚአብሔርም በዳግም ምጽዓት ጊዜ ኃጥኡን ከጻድቁ በእውነተኛው ፍርዱ የሚለይ መሆኑን። # መሬት (# አፈር):- በእግዚአብሔር ታጋሽነት ይመሰላል። መሬት ጥቁር፣ ቀይ፣ ወፍራም፣ ቀጭን ፣ ኃጥእ፣ ጻድቅ ሳትል ሁሉንም ችላ ትኖራለች ፈጣሪም እንዲሁ በማንነታችን ሳይለየን የሚታገሰን መሆኑን።ነው እግዚአብሔር ለንስሐ ያብቃን ቃሉን ሰምተን 30-60-100 እንድናፍራ ያድርገን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን @mahetotorto @mahetotorto @mahetotorto @mahetotorto 336 views21:21