Get Mystery Box with random crypto!

ማህበረ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetewahdo — ማህበረ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahberetewahdo — ማህበረ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @mahberetewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 286
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
ይህ ቻናል
#መንፈሳዊ_መዝሙሮች
#መንፈሳዊ_ጽሑፍ
#ቅዱሳንን_እንወቅ
#የታላላቅ_መንፈሳዊ_ጉባኤ_ማስታወቂያ
#የመንፈሳዊ_ጉዞ_ማስታወቂያ ስለሚቀርብበት ተቀላቀሉን
የጉዞ ማስታወቂያ በቻናሉ እንዲተዋወቅላቹ የምትፈልጉ ከታች ባለው አካውንት ይላኩልን

#ሐሳብ_አስተያየት_ካላቹ
☞ @Mahletay11

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 19:32:58 "እንደ ሞተ ሰው ሁን"


❖ ከወንድሞች አንዱ ወደ አባ መቃርዬስ መጥቶ " አባክህ ለህይወቴ የሚሆን መመርያ ስጠኝ" አለው ፡፡ አባ መቃርዬስም ያንን ወንድም ወደ መቃብር ሂድና በሙታን ላይ ክፋ ነገር አድርግባቸው፡፡ ብሎ ላከው ሰውየውም በሙታኑ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመሳደብ የተላከውን ፈፅሞ መጣ ፡፡ " አባ መቃርዮስም ምን አሉህ ? ሲል ጠየቀው " ያም ወንድም "ምንም አላሉኝም " ብሎ መለሰ ፡፡ በነጋታውም ተመልሰህ ናና አመስግናቸው አለው፡፡ በነጋታውም ያ ወንድም ወደ መቃብሩ ስፋራ ተጉዞ ሙታኑን " ሐዋርያ ፣ ቅዱሳን ፣ጻድቃን ፣ እያለ አመሠገናቸውና ተመለሰ ፡፡ መቃርዮስም " ምን መለሱልህ አለው" ምንም አለ ፡፡" መቃርዮስም " ስትሰድባቸው ፣በድንጋይ ስትመታቸው ፣ ስታመሰግናቸውም ፣ ስታወድሳቸው ፣ ምንም አልመለሱልህም ፡፡ አንተም ለነፋስህ ድህነት ከፈለግክ እንደ "ሞተ ሰው ሆነህ ኑር" ፡፡ ሰዎች ክፋ ቢያደርጉብህም ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ አለው ፡፡፡

ወዳጄ ሆይ የታላቁን አባት ምክር ልብ አልክን ? የሚሰድብህንና ድንጋይ የሚወረውርብህን እንዴት ማለፋ እንዳለብህ ተማርክ ? የሚያመሰግኑህንና የሚያወድሱህን እንዴት መቀበል እንዳለብህ አስተዋልክ ?

☞ ቀልብህን የሚቀሙህን ብዙ ሰዳቢዎች አሉብህ ፡፡ የሚያስጎነብሱህ ብዙ ድንጋይ ወርዋርዎች አሉብህ ፡፡
☞ አንዱ ድህነትህን እያነሳ ያሸማቅቅሀል ፤ሀብት የሌለህና ገንዘብ መቁጠር ያልቻልከው የማትረባ ስለሆንክ ብቻ እንሆነ በማሰብ ያሳንስሀል
☞ በምግባርህ የሞትህ እንደሆንክ እየጮኸ ይነግርሀል
☞ ሃይማኖትህና ኢትዮጲያዊነትህ ለድህነት አስተዋፅኦ እንዳደረገና ማንነትህ ራሱ የተዋረደ እንደሆነ በመንገር ተፈጥሮህን " ንቀህ "አርቴፋሻል እንድትሆን ኦርጅናልነትህን አርክሰህ ፌክ እንድትሆን ይሰብክሃል፡፡
☞ በዘር ገመድ ተብትበው ከወንድምህ ጋር የሚያናቁሩህ ሃይማኖትህንና ሰብአዊነትህ ሳይቀር በዘረኝነት ሰፌድ የሚያበጥሩ ድንጋይ ወርዋርዎችን እንዴት ይሆን ያለፋካቸው ፡፡
☞ ጾምህን የሚያንቋሽሹ ፣ ሱባኤህን የሚረብሹ ፣ ጸበል መጠጣትህን ፤እምነት መቀባትህን የሚያንሻፋፉ ፤እግዚአብሔር በሞተ ነገር ላይ ታሪክ እንደሚሰራ ስትነግራቸው የሚስቁ ፤ በሰማይ ህይወት አለ ስትላቸው በሙት አምራቸው የሚሳለቁ ፤ይልቅ ዓለምህን ቅጭ ጊዜህን ተጠቀምበት የሚሉ አለማውያንና ማንነትህን ለማርከስ ማንነታቸውን ለማንገስ የሚወረውሩት ጥቁር ድንጋይ አቁስሎህ ይሆን ????

ወዳጄ ሆይ ታላቁ አባት እንዲህ ይልሃል ለስጋውያን ለስሌታውያን እንደ ሞተ ሰው ሁን !!!!
☞ ደግሞስ ገና ልትሰራ የምትችለውን ገና በልዑልነትህ ንጉስ ብለውህ ገና በወጣትነትህ ጻዲቅ አድርገውህ ገና በተማሪነትህ ረብኒ ብለውህ ዳዴህን ሳትጨርስ የአትሌትነት ማዕረግን ሰጥተውህ በዲያብሎስ መዝሙር ከፋ ከፋ በጣሙን ከፋ ከፋ ሗላ ስትወድቅ አጥንትህ እንዳይተርፋ ሰቅለው በአፋጢምህ የሚደፋህን አድር ባዮችና ህሊና ቢሶች እንዴት አልፈሀቸው ይሆን ? ለእነርሱም ወሬ መንኩሰህ እንደ ሞተ ሰው ሆንክን ??

☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ትዳር አለህ ፡፡
☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታድነው ህይወት አለህ
☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምታጠነክረው ወዳጅነት አለህ
☞☞ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ የምትሰራው እልፋ ስራ አለህ ፡፡

✞ ደግሜ ደግሜ እልሃለሁ የታላቁን አባት ቃል ተውሼ ለእነዚህ እንደሞተ ሰው ሁን!!!!

እንደ ሞተ ሰው ሁን እንጂ ሙት ሁን አልተባልክም ፤ እንደ ሞተ ሰው ሆነህ በግብርህ ሕያው ሁን እንጂ ሙት አትሁን፡፡

" ሀዋርያው እንዳለው አንተ ለዚህች አለም ሙትባት ይህች አለምም በአንተ ዘንድ የሞተች ትሁን ፡፡፡
"" እንደሞተ ሰው ሁን """
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
33 views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 16:52:58 ✥ የሰማይም ሰባት ጊዜ መከፈት ✥

በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ምርምር መሠረት በዓመት ውስጥ ሰባት ጊዜ ሰማይ ይከፈታል። ይህም የሰማይ መከፈት ይባላል። በነዚህ ዕለታት የፈጣሪ በረከት ለምድር በምህረት ይታደላል። ነገር ግን በተሰበረ ልብ መንበርከክን ይጠይቃል። የምህረቱ ብዛት ጥልቀቱ የማይለካው ፈጣሪ ምንም እንኳን የይቅርታ እጆች በየዕለቱ የተዘረጉ ቢሆንም ያስቀመጠውን መርህ የሰማይ መከፈት ዕለታት ራሱን ለማደስ በንስሐ ቢቀርብ ምህረት ይጎበኘዋል። ሰባቱ የሰማይ መከፈት ዕለት የሚባሉት።

1-ጥቅምት ሃያ/20/
2-ታህሳስ አስራ ሁለት/12/
3-መጋቢት ሃያ ስድስት /26
4-የካቲት አራት/4/
5-ግንቦት አስራ ስምንት/18/
6-በሐምሌ አስር /10/
7-ጶግሜ ሁለት /2/ ናቸው።

ሊቃውንት እንደሚሉት ፈጣሪ የስነ-ፍጥረት መጀመሪያ ስድስቱን ቀናት እና ለዕረፍት እንድትሆን የተፈጠረችውን ሰንበትን በማሰብ በዓመት ሰባት ቀን ምህረትን ያዘንባል። በእነዚህ ዕለታት ፀበል መጠመቅ ንስሃ መግባት የተቸገረንን መጠየቅ ከሰማያዊ መለኮት ረድኤት በረከት ያስገኛሉ።

ምንጭ:- ከመስፍን ሰለሞን " ሰባት ቁጥር " ከተሰኘው መፅሐፍ የተወሰደ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን

ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
3.2K views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:12:53
73 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:54:09
70 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:14:56
66 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:14:53
57 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:53:16
59 views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ