Get Mystery Box with random crypto!

የኛ tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ m_b_lovestory — የኛ tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ m_b_lovestory — የኛ tube
የሰርጥ አድራሻ: @m_b_lovestory
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 124
የሰርጥ መግለጫ

╭─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╮
እንኳን
:¨·.·¨: 🛐ወደ
 `·. . የኛ tube ቻናል መጡ
╰─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╯


⏰◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉ 👨
🙄አላማችን የተማረና የሚያገናዝብ ዜጋን መፍጠር ነው,,,,,,,,,,,ቀደምት ነበርን እንደነበርንም በተግባር አናስመሰክራለን🙏
Channal ፦ @M_B_Lovestory

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-01 21:39:07 :
:
;;;;; ቃል ብንገባስ!::::::

በአንድ ትልቅ የገበያ ማዕከል ውስጥ እየተዘዋወርኩ ነበር።ገንዘብ ተቀናይዋ ከአንድ 5 ወይም 6 ዓመት ከሚሆን ህፃን ጋር እተከራከረች ተመለከትኩ።ለማሳመን የምትሞክረውን ጥረት አይቼ ተሳብኩ።"አዝናለሁ ይህን አሻንጉሊት ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ የለህም"አለችው።ልጁም የሴትዬዋን ሐሳብ ባለመቀበሉ ይመስላል ወደ እኔ ዞር አለና፦ "ጋሼ ይህ የያዝኩት ገንዘብ አሻንጉሊት ለመግዛት አይበቃም?" አለኝ።


ገንዘቡን ቆጠርኩትና በአሻንጉሊት ላይ ከተለጠፈው ዋጋ ጋር አመሳክሬ የያዘው ብር በቂ እንዳልሆነ ነገርኩት።ቢሆንም ልጁ አሻንጉሊቱን አሁንም በእጁ እንደያዘው ነው።


ሁኔታው ገርሞኝ ነበርና ተጠግቼ "አሻንጉሊቱን በጣም ወደድከው እንዴ ማሙሽ?" አልኩት። "አይ እህቴ ይህን አሻንጉሊት እጅግ በጣም ትውደዋለች ለልደቷ ቀን ልሰጣት ፈልጌ ነው" አለኝ። "ዛሬ የእህትህ የልደት ቀን ነው?" ብዬ ጠየኩት። "አይደለም አሻንጉሊቱን ለእናቴ አሰጣትና ለእህቴ ለልደት ቀኗ ታደርስለኛለች ብዬ አስቤ ነበር"አለኝ።ይህን ሲል አንዳች የሀዘን ድባብ በልጁ ላይ ይነበባል።እኔም መጨረሻውን ለመስማት ጓጓሁ።ቀጠለና፦ "እህቴ ወደ አምላኬ ሄዳለች። አባቴ እንደ ነገረኝ ማሚም ወደ አምላኬ ልትሄድ ነው እና አሻንጉሊቱን ለእህቴ ታደርስልኛለች ብዬ አስቤ ነበር" አለኝ።ልቤ መምታቱን ያቆመ መስለኝ።


ሕፃኑ ልጅ ትክ ብሎ አየኝና ቀጠለ፦ "ይህን አሻንጉሊት ገዝቼ እስክመለስ ድረስ ማሚ እንድትጠብቀኝ ለአባዬ ነግራዋለሁ"ብሎ ከኪሱ ፎቶግራፍ እያወጣ "ይህን ፎቶግራፍ ለእህቴ እልክላታለሁ እናም እህቴ ለዘላለም አትረሳኝም አለኝ።ዞረብኝ ፎቶግራፉ ሕፃኑ እየሳቀ ያሳያል።

"እናቴን በጣም እወዳታለሁ።እንድትለየኝ አልፈልግም ግን አባቴ እንደነገረ ኝ ማሚ ከእህቴ ጋር መሆን አለባት።

ለእህቴ ታስፈልጋታለች"አለኝ።በሀዘኔታው ዓይን አሽንጉሊቱን በድጋሜ በስስት ተመለከተው።

"እስኪ እንደገና ዋጋውን እንየው ምናልባት የያዝከው ገንዘብ ሊበቃ ይችላል እኮ" አልኩት።

"እሺ"አለኝ።


በፍጥነት ቦርሳዬን አወጣሁና ሳያየኝ ጥቂት ገንዘብ አውጥቼ ከእርሱ ገንዘብ ጋር ቀላቅዬ መቁጠር ጀመርኩ።አሁን በቂ ገንዘብ ተገኘ።አሻንጉሊቱን መግዛት ይቻላል።እንዲያውም መልስ ይኖረዋል።


ያም ልጅ፦"አምላኬ ሆይ ይህን አሻንጉሊት የምገዛበት በቂ ገንዘብ ስለ ሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ"አለ።ወደ እኔ ዞር አለና…"ትናንትና ማታ ከመተኛቴ በፊት አምላኬን ለአሻንጉሊት መግዣ የሚሆን ገንዘብ እንዲሰጠኝ ጠይቄው ነበር።እናም ሰምቶኛል በቃ ማሚ ለእህቴ ትሰጥልኛለች"አለ።


"ለማሚ ደግሞ ነጭ አበባ ለመግዛት ፈልጌ ነበር።ታዲያ በተረፈኝ ብር አሁን መግዛት እችላለሁ።ማሚ ነጭ አበባ ትወዳለች።አሁን ሁለቱም መግዛት ችያለሁ አለ በፈንጠዝያ።


ከሁለቱ ቀናት በፊት በአካባቢው እየታተመ ከሚወጣው ጋዜጣ ላይ ያነበብኩት ዜና ትዝ አለኝ።አልኮል ያለ ልክ ጠጥቶ ሲያሽከረክር የነበረ አንድ ግለሰብ የገጫትና መኪና ምስል አስታወስኩ።

መኪናውም ስታሽከረክር የነበረችው ሴት አጠገብ ትንሽዬ ልጅ አለች።አደጋው በደረሰበት ቅፅበት ሕጻኗ እንዳረፈችና የእናትዬው ሕይወት አስጊ ሁኔታ ላይ እንደነበር ያነበብኩት ትዝ አለኝ።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ቤተሰቦቿ ሕይወት ቀጥል ማሽኑን ለማስቆም እንዲወስኑ ተገደው ነበር።ለምን? ቢሉ ሴትየዋ ከኮማ መንቃት አልቻለችምና ነው።ራሴን ጠየቅኩ…እና ይህ ሕፃን

የዚህ ቤተሰብ አባል ነው ማለት ነው?


የምገዛውን ጨርሼ ወጣሁ።ሕጻኑ ግን በጭራሽ ከአእምሮዬ ሊወጣ አልቻለም።


ከሁለት ቀናት በኋላ ሌላ ጋዜጣ አነበብኩ የዚያችን ሴት ሕልፈት አነበብ ኩ።የዚያችን ሴት ህልፈት አወቅሁ።ነጭ አበባ ታቅፌ ወደ መቃብር ስፍራ ከመሄደ ራሴን መከልከል አልቻልኩም።በቀብሩ ስፍራ የዚያች የአደጋው ሰለባ ሴት እስክሬን ከአንድ ነጭ አበባ ጋር አየሁ።አሻንጉሊቱና የገበያ ማዕከሉ ውስጥ ያገኘሁት ውብ ሕፃን ፎቶግራፍ ደረቷ ላይ ተቀምጠዋል።የቀብሩ ሥነ-ሥርዓቱ ተጥናቆ ስፍራውም ስለቅ ዓይኖቼ ከማንባት አልቦዘኑም።


ለመገመት አስቸጋሪ ነው ።ሕጻኑ ለእናቱና ለእህቱ ያለው ፍቅር የሚደንቅ ነው።በአንድ ድንገተኛ ቅጽበት ያለ ልክ አልኮል የጠጣ አሽከርካሪ በፈጠረው ተመልሶ የማይታረም ስህተት ፍቅሩ ተነጠቀ።ዛሬ እናትና እህቱ አጠገቡ የሉም።

ይህን ልብ የሚሰብር ታሪክ የሰማ ሁሉ "ላይጠጣ ከጠጣ ደግሞ ከልክ ላያልፍ "ቃል ይገባል ብዬ አስባለሁ።


የዚህ ሕጻን ነገር ልቤን በረበረው።የዕንባዬን አለት በሕፃንነቱ በትር መታው።አለቀስኩ።እንባዬ መጀመሪያ ወደ ውስጥ ቀጥሎ ወደ ውጭ ፈሰሰ።

ማታለል አልፈለግሁም በሰው ለቅሶ ለእኔ ሙት አላለቀስኩም። ለዚያ ሕጻን ያለኝን ስሜት በዕንባ ገለጥኩት። ብዙ ዓይነት ስሜቶች ተፈራረቁብኝ።

በራሴ ላይ ያነጣጠርኩትን አጉሊ መነጽር አነሳው።ሁለት ነገሮች በዋናነት ታወሱኝ።

ምን ምናልባት ነገ እቀጥላለሁ ለአሁን መልካም ምሽት

@mekdiclassic
57 viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 21:35:49 ማንኛውም አሰተያየት ካላችሁበዚ ልነግሩን ትችላላቹ
https://t.me/+jvS8UCJcbqI3ZWY0
52 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 20:59:37 Wede yechannelacn teketayoce enanetan yazenanal belan basabenawe nger kece belenale getem bevice lekefawe
fkrleyazaw
fkrgawen lata
Familwen lemewade
beraso mkneyat saw lata bemulu mret yemebale nger azegajetenale yenaneta temeracoce
@binayeeeee
@mekdiclassic
100 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 21:59:23 #ተሳስተሻል
:
:
ሻማ ስትለኩሺ ኬክም ስትቆርሺ ላየሽ ሰው በሙሉ፣
የምጓጓለት ቀን ልደቴ ነው ዛሬ እያልሽ ነው አሉ።
:
:
እውነት ነው ወይ ውዴ እንደዚያ ብለሻል?
የሰማሁት ነገር ትክክል ከሆነ በጣም ተሳስተሻል።
:
:
ምክንያቱም ውዴ
እንደ ሾላ ጥላ እንዲያ ተንዠርግጎ ሀዘን በኔ አጥልቶ፣
ፍቅርን ተርቦ እኔነቴ ዳምኖ ልቤ በቁም ሞቶ፣
በሁሉም አቅጣጫ ከቦኝ ባለ ጊዜ ዕፀፅ በበረሀ፣
ነብስ የዘራሁትኝ ጠጥቼ አይደለም ወይ ከልብሽ ምንጭ ላይ የህይወትን ውሀ።
:
:
መውደድን ተርቦ ባለም ላይ ሲዳክር ለነበረው ልቤ፣
ዕፁብ የሆነውን የልብሽን ፍቅር ለልቤ መግቤ፣
ደመነፍሴን ሆኜ ትላንት እንዳላደርኩ ተስፋ ባጣ ግርጌ፣
ታውቂ የለም እንዴ ዳግም ሰው እንደሆንኩ ትንፋሽሽን ምጌ።
:
:
በውሀ ላይ ስሮጥ አንዳች ለማልጨምር ሁሌም ሆኜ እዛው፣
ላላተርፍ ነገር ጉልበቴን ስጨርስ ድካሜን ሳበዛው፣
ያለምንም ስስት ኑሮዬ እንዲሰልጥ ህይወቴ እንዲቀና፣
አንቺ አይደለሽ እንዴ ደርሰሽ ያሳየሺኝ የፍቅርን ጎዳና።
:
:
እውነት ለመናገር ብሶት እየጫረች ዐለም በፍዳዋ ደርሳ እንዳትማግደኝ፣
በዚች ቅድስት ዕለት ያንቺ መወለድ ነው ዳግም እንደገና እኔን የወለደኝ።
:
:
ውሉ ጠፍቶት ልቤን ህይወት በኔ ሲከር፣
አንቺን ባላገኝሽ ማን ይወልደኝ ነበር።
:
:
እናልሽ እንቁዬ
ገና ከጅምሩ ልደቴ ነው ዛሬ ማለትሽን ስሰማ፣
ተሳስተሻል ያልኩት ምንም ሳላቅማማ፣
ባንቺ መወለድ ውስጥ ዳግም እንደገና እኔ መወለዴን፣
መዘንጋትሽን ሳውቅ ቢቆርጠኝ ነው ሆዴን።
:
:
እናም ካሁን ወዲ
ይህን ቀን ለማክበር ሽር ጉድ ስትዪ፣
ከሁሉ አስቀድመሽ ይህቺን አስተውዪ።
:
:
በፍቅርሽ እስትንፋስ በተቸረሽ ጥበብ በትንሳዬሽ ጉልበት፣
ባንቺ መወለድ ውስጥ ዳግም እንደገና ስለተወለድኩኝ ሞቼ ካለሁበት፣
ዛሬ ቀን ምንድነው ብሎ ለጠየቀሽ እንዲ ብለሽ አስረጂ፣
ልደቴ ነው አትበዪ ያንቺ ብቻ አይደለም ልደታችን እንጂ።
113 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 08:17:19
92 views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 08:37:35 አሜን በይ አደራ

ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።

ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።

ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።

በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።

እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ

የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።

የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።

ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።

ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።
አሜን በይ
106 views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 13:33:08 Melaka yesetoce kane
113 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 13:32:24
111 views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ