Get Mystery Box with random crypto!

💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌

የቴሌግራም ቻናል አርማ luvmessageee — 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ luvmessageee — 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌
የሰርጥ አድራሻ: @luvmessageee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 91
የሰርጥ መግለጫ

😍 melake yeflgachiwetn 😘
💖 Lakulne 👉 @Mdryhbdddbot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-06 02:20:46 https://t.me/+TJDMUgYYSMZhOWU0
98 viewsHabti Med, 23:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 23:03:12 ነግሬሽ ነበረ

ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።

ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።

ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

በላይ በቀለ ወያ እንደፃፈው


@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
88 viewsÃM€Ñ, 20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 12:44:12
63 viewsÃM€Ñ, 09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 14:04:02 (አሌክስ አብርሀም)
ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
https://t.me/luvmessageee
427 viewsÃM€Ñ, 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 13:31:36 ሲከፋህ መኖርህ ትርጉም ያጣ ይመስልሀል እንጂ ያንተ መኖር የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ባዶነት ሁሉም ሰው ይሰማዋል ወሳኙ ነገር በዛው ቅፅበት ያንተ ወደዚህ አለም መምጣት ህይወታቸው ላይ አንድ ሀይል የሚጨምርላቸው ሰዎች አሉ።

በፍፁም አላስፈልግም እንዳትል! ወዳጄ ታስፈልገናለህ! እህቴ ታስፈልጊናለሽ!

ደማቅ ውሎ ተመኘንላችሁ
@yenagtm
@yenagtm
75 viewsÃM€Ñ, 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 21:13:34 በዛ ዘመን አባቴ በህዝብ ስልክ ተጀናጅኖ እናቴን ያገባል me with a smart phone is still single
https://t.me/luvmessageee
566 viewsÃM€Ñ, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 10:32:44 sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it. https://video-c5.xyz/2921956050813737/
111 views𝐀𝐌𝐄𝐍, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 13:08:51 ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ


ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡

ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡

እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡

እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

በላይ በቀለ ወያ

@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm
137 viewsÃM€Ñ, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-14 13:34:42
138 views𝑚𝑒𝚛𝚘𝚗, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-13 16:13:26
404 views𝑚𝑒𝚛𝚘𝚗, 13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ