Get Mystery Box with random crypto!

እቀፈኝ የሐምሌ ነጎድጓድ ገፍትሮ ሳይጥለኝ የጥቅምቱ ነፋስ አጥንቴን ሳይሰብረኝ አዎ'ና እቀፈኝ! | 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌

እቀፈኝ

የሐምሌ ነጎድጓድ ገፍትሮ ሳይጥለኝ
የጥቅምቱ ነፋስ አጥንቴን ሳይሰብረኝ
አዎ'ና እቀፈኝ! ትንፋሽህ ይሙቀኝ።
የክረምቱ ብርድ ቆፈን ሳያሲዘኝ
ና ድረስና ከ'ቅፍህ ሸሽገኝ።
አዎ ና እቀፈኝ.......
ናፍቆትህ ይሙቀኝ
..............እንደ ግንቦት ፀሐይ እንዳ'በቦቹ እንደ ወቅቱ ፀደይ ፍቀድልኝና ላብብ ከልብህ ላይ፡፡

መኳንንት
@yenagtm
@yenagtm