Get Mystery Box with random crypto!

ይሄን የሚያህል ባንክ ይህን የሚያጣራ ባለሙያ አጥቶ ነው የመጀመሪያው ምስል አድባር ቁ.3 በ | LOONY™️

ይሄን የሚያህል ባንክ ይህን የሚያጣራ ባለሙያ አጥቶ ነው

የመጀመሪያው ምስል አድባር ቁ.3 በ አርቲስት Mezgebu Tesema የዘይት ቀለም በሸራ ላይ የተሰራ ስእል እና ከውስጡ የተወሰደ ገፅ ባህሪ ያሳያል ቀጣዩቹ ደሞ ለ #Commercial Bank of Ethiopia ህንፃ ማስዋቢያ "ሀብት ካለ በሰማይ መንገድ አለ" በሚል ርእስ የተሰራ ሀውልት ንድፍ እና ገፅታ ያሳያል።

ይህን መረጃ ከአርቲስቱ የቅርብ ወዳጆች ያገኝን ሲሆን የነዚ ሁለት ስራዎች መመሳስል በህግ ለማረጋገጥ ማስረጃዎች እየተሰባሰቡ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ።

እነዚህ ሁለት ስራዎች በምስሉ ላይ እንዲሚታየው መመሳስል እና የቅጅ ያህል የመዛመድ አላችው። ይህም በሃገራችን የፈጠራ ባለመብትነት ህግ ያለ ባለሙያው ፈቃድ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በማንኛውም መልኩ ማባዛትም ሆነ መገልበጥ በህግ አግባብ የሚያስጠይቅ ይሆናል ። እኛም ግዜያችንን ሰተን ጉዳዮን ልናየው ወደናል ። እርሶስ ምን ይላሉ ይሄን የሚያህል ባንክ ይህን የሚያጣራ ባለሙያ አጥቶ ነው ?

አርቲስቱ ስራውን ቀድመው ስለመስራታቸው የሚያሳይ ማስረጃዎችን ከታች አያይዘናል ።
https://telegra.ph/ማስረጃዎች-02-22

#Share