Get Mystery Box with random crypto!

'…ትናንት በራያ ግምባር ላይ የሚገኘው የምሥራቅ ዐማራ ፋኖን ህዝቡ ኮቾሮ ይገዛለት ዘንድ መለመኔን | ልሳነ ዐማራ

"…ትናንት በራያ ግምባር ላይ የሚገኘው የምሥራቅ ዐማራ ፋኖን ህዝቡ ኮቾሮ ይገዛለት ዘንድ መለመኔን ታስታውሳላችሁ። የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ እነ ምሬ ወዳጆን በጎበዜ ሲሳይ ሚዲያ ላይ አይቼ ፈልጌ ያገኘሁትም እኔው ነኝ። የጎደላቸውን ነገሩኝ። ሕጋዊ እስከሆኑና መንግሥት እስካወቃቸው ድረስ ቢረዱ መልካም ነው ብዬም እንዲረዱ አድርጌያለሁ።

"…ዛሬ ታዲያ ምን ብሰማ ጥሩ ነው? እኔ እንደ ሙጂብ አሚኖ እስላም መርጬ የምረዳ መስሏቸው ጉዳዩን ከኃይማኖትም ጋር አጋብተው ጠባብ አዕምሮ ያላቸው ጎጠኞች ዘመድኩን እነ ምሬን እንዲረዱ ያደረገው እነ ጀግናው አርበኛ ፋኖ ሃሰን ከሪሙ እንዲረዱ ያላደረገው በሃይማኖት ምክንያት ነው። እሱ ኦርቶዶክስ እሳቸው ሙስሊም ስለሆኑ ነው ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ታይተዋል። ይሄ ነውር ነው። የእኔን አስተዳደግ ያለማወቅም ነው። የሐረር ሰው በሃይማኖት አይታማም። ነውረኛ ሁላ።

"…ደግሞም እኮ ምሬ ወዳጆ (የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ ዋና አዛዥ) ሲሆን ከድር ሰይድ ደግሞ (ምክትል አዛዥ) እኮ ነው። መሰረት ጫኔ (ሃብት አፈላላጊ)። በምሬና በከድር የሚመራው ፋኖ ወሎ ቤተ ዐማራ የንጉሥ ሚካኤል ልጆች ናቸው። እስላም ክርስቲያን ሳይሉ እየተዋደቁ ያሉ ናቸው። ሆኖም ግን እነ ወሎ ኬኛ ደስተኛ አልሆኑም። አብደዋል። ጉዳዩን አጡዘውታል። እሱን ነው ለማክሸፍ ዛሬ የተገለጥኩት።

"…እኔ +251920214440 ሃሰን ከሪሙ ጋር ደውያለሁ። ስልኩ ዝግ ነው። ቀጥሎ በዚህ ስልክ ደውል ተብዬ ደውዬ +251911097899 አንዲት ሴት ደውለው የማውቀው ነገር የለኝም ብለውኛል። ከዚያ በዚህኛው ስልክ ደውዬም +251912197692 ስልኩ ዝግ ነው። የደወልኩት የወሎ ዐማራ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ነው ተብሎ የተላከልኝን ለማረጋገጥ ነበር። እኔ ደግሞ ሳላረጋግጥ አላወራም። አይደለም እንዴ?

"…ከመንግሥት ጋር ዘመዴ ጠበኛ ስለሆነ ብሎ ፖለቲካ መሥራት ይደብራል። እኔ ሽመልስ አብዲሳን እስከ ዶቃ ማሰሪያው እየነገርኩት በኦሮሚያ ለተፈናቀሉት ዐማሮች በጎፈንድሚ 3 ነጥብ 2 ሚልዮን ዶላር፣ በሃገርቤት 48 ሚልዮን ብር ሰብስቤ ሳድል ትብብር ለኮሚቴው የሰጠው ሽመልስ አብዲሳ ነው። በዜና ሁላ ተሠርቷል። እና እኔ ዐቢይን ስለተቸሁ ሃገሬን መርዳት፣ ህዝቤን ማገዝ አልችልም እንዴ? ሃገር እኮ የጋራ ነው። ዐቢይን በኩርኩም እያልኩትም የተፈናቀለ ብረዳ ፀቡ የእኔና የዐቢይ የግል ጉዳይ እንጂ የተራበ ስለተረዳ እንዳትረዳ አይለኝም። ቢለኝም አልሰማውም። ነጋዴ ብሆን ንግድ ፈቃዴን ይወስድ፣ ይከለክለኝ ይሆናል እንጂ እኔን ስለምትተች የራበ አታብላ አይለኝም። ባይሆን አዲስ አበባ ብኖር ኖሮ፣ አጠናግሮ፣ አጠናግሮ፣ ጠፍጥፎ፣ እብድ የለሰነው ልስን ሊያስመስለኝ ይችላል። ወይ ደግሞ ቃሊቲ ሊወረውረኝ ይችላል። ከራራልኝ ደግሞ እንደ ሃጫሉ ሁንዴሳ በጊዜ ሊሸኝ ይችል ይሆናል እንጂ ሃገርህን አትርዳ ሊለኝ አይችልም።

"…እናም ምን ለማለት ፈልጌ ነው። በጦር ግምባር ለሚዋደቁ የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ የቻልኩትን ባደርግ ሰይጣንና ወያኔ ይወበሩ፣ ይናደዱብኝ ይሆናል እንጂ፣ ኦነግ ሄጵ ሊልብኝ ይችላል እንጂ ሌላ ሰው የፈለገ ቢጠላኝ ይናደድብኛል ብዬ አላስብም። ጭቅጭቅ ንትርካችን ይቀጥላል። ሃገር ማዳኑም ይቀጥላል። እኔ እደሆን መቃብር ካልወረድኩ በቀር ወይ ፍንክች። እገሌን ላስደስተው፣ ለእገሌ ላቃጥር የምል ኮልኮሌ ካድሬ እኮ አይደለሁም። ሰምተሃል ምድረ ገተት ሁላ…!!

"…በወሎ ሦስት የዐማራ ፋኖ አደረጃጀት እንደለ ሰምቻለሁ።
1ኛ፦የምስራቅ አማራ ፋኖ
2ኛ፦ የወሎ ፋኖ
3ኛ፦ የቤተ አምሐራ ፋኖ በእኔ አይን ሁሉም አንድ ናቸው። አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ እንዲረዳ አድርጌአለሁ። ቀጥሎ የእነ ሃሰን ከሪሙን፣ ከዚያ ቤተ ዐማራን እንዲረዱ እናደርጋለን። ይሄ ቃሌ ነው። ይሄን የማደርገው ለራሴ ስል ነው። ዐማራ ነፃ ያወጣኛል። ሃገሬም ያስገባኛል ብዬ አምናለሁ። ይህን ስል የሚከፋህ ካለህ ደግሞ በአናትህ ተተከል። ምን ታመጣለህ ምደረ ዱቄታም…!! ሰረሰርህ ይውለቅና በአንተ ቤት ሴራ አግኝተህ ሞተሃል። እኔ እኮ ዘመዴ ነኝ። የሀረርጌው መራታ፣ ውኃ ጠብሼ ቀቅዬ የምበላ አራዳ፣ ምደረ ሰገጤማ አይሸውደኝም። እንከፍ ሁላ…!!

"…አሁን የእነ ሃሰን ከሪሙን ስልክ ስጡኝ…!! ወይም አገናኙኝ። አበቃ። ከዚያ ሴራው ይከሽፋል።

"…ካነበባችሁ በኋላ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። የኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ሰዓታችንም እየደረሰ ነውና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ።