Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | የፍቅር ጀማሪ 😘😍

​​​​ ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

Part 26

... ጌዲዮ ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ
ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ
ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ
የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው
ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና
አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ
ነች........
.....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ
የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው
ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን
አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ
ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን
መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ
ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ
ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው
ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ
የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን
የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ..........
.......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ
ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት
አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት
ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች
ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ
አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው
ጥላሁንስ ቢሆን........
.........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ
ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ
አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ
እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም
ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን
እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት
ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው
ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ
የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን
መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ
በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ
ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ
ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም
ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን
ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል
........
........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ
አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ
ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና
ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው
በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው
በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም
ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ
አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት
ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው
እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው
ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው
አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ
መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ
አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር
ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ
ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው
መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው
መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ
ብለው አስታወሱ............
........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት
ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል
በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው
ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት
አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው
ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ
የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት
መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት
አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡ክፍል 27 ከ70 ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

❥..................❥

••●◉Join us share◉●••
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━

@LovestoryB_wiz_H
@LovestoryB_wiz_H

For any comment
@Romio_Bina