Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | የፍቅር ጀማሪ 😘😍

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

Part 24

... እየውላቹ ይህ ዜና ለናንተ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ግዴታ መናገር ስላለብኝ ስሙኝ ጌዲዮ የጭንቅላት እጢ ታማሚ ነው መቅደስ አፏን ይዛ እየተንቀጠቀጠች ምን አለች አዎ ህክምናውን በጊዜ ጀምሮ መዳኒት ስላልወሰደም በሂወት የመኖር ጊዜውን አጥቦታል መቅደስም ሆነች አባቷ እንባቸው ድንገት እንደሚጥል በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ዱብ ዱብ ይል ጀመር መቅደስ በልህ ድምጿን ከፍ አድርጋ እና ይሞታል ልትለኝ ነው አለችው ዶክተሩም አላልኩም የምትችሉት ከሆነ አንድ እድል አላችሁ አላቸው አባቷ እንደምንም አረጋግቷት ምንድነው ንገረን ብቻ ጌዲዮ ይዳን እንጂ የሆነውን ይሁን ለመፈፀም ዝግጁ ነን አሉ ባስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት መቅደስ አይሆንም ብላ ይበልጥ ጮኸች ችግሯ ህመሟ ቢገባውም መረጋጋት ባለመቻሏ ዶክተሩ ተናደደ መቅደስ አዳምጪኝ ቀዶ ጥገናው እዚህ ሀገር አይሰጥም ይህ ማለት በዚህ አራት ወር ውስጥ ካገር ወጥቶ ቀዶ ጥገናውን ካላደረገ በሂወት መኖሩ አስጊ ነው ለህክምናው ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብሎ ሃሳቡን በቁጣ ገልፆ ቁና ተንፍሶ ላንዴ ዝም አለ መቅደስና አባቷም በህልማቸው እስኪመስላቸው ደርቀው ቀሩ ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ..........

......ከወጡ ቡሀላ መቅደስ ተዝለፍልፋ ወደቀች ነርሶችም ተሯሩጠው አንስተው አስተኟት ስትነቃም ሁሉም ቤተሰቦቿ ተሰብስበው ነበር አባቷ ነግሯቸው ስለነበር ሁሉም አይናቸው በንባ ብዛት በርበሬ መስሎ ነበር እማ ሁለት ሚሊዮን ያስፈልጋል አሉ እኮ አለቻት የቤተሰቦቿን አይን አይን እያየች እህቷም እሷን ለማፅናናት ያንቺ እንዲህ መሆን እኮ ብር አይሆንም ይልቅ ብሩን እንዴት ማግኘት እንዳለብን ብናስብ ነው የሚሻለው ስትል እንዴ ከየት ነው የሚመጣው አለች መቅደስ ቀጥሎም ቅብጥብጡ ወንድሟ ሲስቱ ተነካሽ እንዴ ሁለት መቶ ሺ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሀገር እንዴት ብለሽ ነው ሳይጨርሰው የሁላቸውም ታላቅ የሆነው በረከት ከየትም ብለን አግኝተን መታከም አለበት እናትየዋም አዎ ቤታችንንም ቢሆን ሸጠን እናሳክመዋለን ማሟያ ደግሞ ሁላችንም አካውንት ያለውን ብር እናወጣለን ካልሞላም ብድር አናጣም የሚል ተስፋ ለመቅደስ ሰተዋት ከዛን ቀን ጀምሮ በየፊናቸው ብሩን ማፈላለግ ጀመሩ ብዙ ወጪ ስላወጡ የሁሉም አካውንት ውስጥ የተገኘው ብር ስድስት መቶ ሺ ብቻ ነበር ቤቱም ያሰቡትን ብር ሊያወጣ አልቻለም........

.........ሌላ ህመም እንዳይሆንበት ስለፈሩ ነገሩን ለጌዲዮ እስካሁን አልነገሩትም እናቱ ግን ቢሰሙም ደጀ ሰላም እየሄዱ ደጅ ከመፅናት ፈጣሪን ከመለመን ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም ዘወትር የመቅደስን ቤተሰቦች ሲያዩ እንዲህም አለ ወይ ይላሉ ጌዲዮንን ለማሳደግ ያዩትን መከራ እሳቸውና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው እንኳን የባለቤታቸው ዘመዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸውም ሰላምታ ሰተዋቸው እንኳን አያውቁም የጌዲዮ እናት ያለፉትን አመታት ሲያስታውሱ ደም እንባ ያለቅሳሉ ቢሆንም ፈጣሪ እንደሰው አይደለም ይኸው እነመቅደስን ሰጣቸው እውነት በዚህ ሰአት ብቸኛ ቢሆኑ ኖሮ ጌዲዮ ነብሱ ባልተረፈች ነበር ግን ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ..........

.......ግን ምንም እንዳሰቡት ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ቤቱንም የሚገዛ አጡ ቢያገኙም የሚጠሩላቸው ዋጋ ለቤቱም ለህክምናውም አይመጥንም በቲቪና በራዲዮንም ማስታወቂያ ሊያሰሩ ቢጠይቁም የጠየቋቸው ገንዘብ ከባድ ነበር በዛላይ ዶክተሩ ያለው ግዜ አጭር ስለሆነ በፍጥነት ፕሮሰስ መጀመር እንዳለበት እየነገራቸው ነው አሁንማ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው የሚገቡበት ጠፍቷቸው ወደፈጣሪ እግዚኦ እያሉ ነው........

.........ሁኔታቸው ግራ ያጋባው ጌዲዮ ቅብጥብጡን ቅዱስ ብቻውን ሲያገኘው ቅዱሴ አለው ወዬ ጌዲ አለው የህክምናውን ውጤት ንገሩኝ ስላቸው ደና ነው አሉኝ ደና ከሆንኩ ለምን አልወጣም ስላቸው አይ ትወጣለህ ይሉኛል ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም ተረብሻችኋል ምን ሆናችሁ ነው በጭንቀት ማለቄ እኮ ነው ሲለው ያው ቅዱስ እስካሁንም ያላወራው አፉን ይዘውት እንጂ ወሬ የሚባል አይደብቅም እናም ምን ባክህ የጭንቅላት እጢ አለበት ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ለዛ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለውን ተፍ ተፍ እያልን ነው ብሎ ካልታከመ መሞቱ እንደማይቀርም ፍርጥርጥ አርጎ ነገረው ጌዲዮ ተስፋ ቆርጦ እና እሞታለሁ አለው አረ ላሽ ትታከማለህ ደሞ ቤታችን ሊሸጥ እየተስማማ ስለሆነ እግዚያብሄር ከረዳን ብሩ ይገኛል ጌዲዮ ከመቅፅበት ህመሙ ተነሳበት...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡ክፍል 25 ከ70 ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

••●◉Join us share◉●••
━━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━━

@LovestoryB_wiz_H
@LovestoryB_wiz_H

For any comment
@Romio_Bina