Get Mystery Box with random crypto!

ፈራጁ አንድ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት የቀረበ ወንጀለኛ በጣም ጎበዝ ጠበቃ ነበረውና ተ | 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

ፈራጁ

አንድ በከባድ ወንጀል ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት የቀረበ ወንጀለኛ በጣም ጎበዝ ጠበቃ ነበረውና ተከራክሮለት ከቅጣት አዳነው ከእስርም ተፈቶ ኑሮውን ቀጠለ ፡፡

ከአመታት በኋላ ይኸው ልማደኛ ወንጀለኛ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀረበ ያን ጊዜ ጠበቃው ሆኖ ተከራክሮ ነፃ ያወጣውን ሰው ግን አሁን ላይ ሊያድነው አልቻለም ምክንያቱም የዛኔው ጠበቃ አሁን ላይ ዳኛ ሆኗልና እናም በወንጀሉ ልክ ፈርዶ ቅጣቱን ሰጥቶታል ፡፡

ፈጣሪም በምድር ሳለን ምንም ያህል ብንበድል ብናጠፋ ጠበቃችን ሆኖ ከችግር ከመከራ ከአደጋ ከፈተና ይጠብቀናል ነገር ግን ጊዜያችን ደርሶ ወደማይቀረው ስንሄድ ግን ዳኛ ሁኖ ይጠብቀናል ፡፡

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር