Get Mystery Box with random crypto!

ባለህ ተደሰት የሆነ እድሜ ስንደርስ ‘እርፍ እንላለን’ የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ብዙዎቻችን ልብ ዉስ | 💔 ስነ ልቦና 💆‍♀

ባለህ ተደሰት

የሆነ እድሜ ስንደርስ ‘እርፍ እንላለን’ የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ብዙዎቻችን ልብ ዉስጥ አለ ፡፡

ለምሳሌ “ልክ ሚስት አግብቼ እንትን መስሪያ ቤት ስገባ እርፍ እላለሁ፣ እንዲህ ሳደርግ እርፍ እላለሁ፡ ጭንቀቴ ይጠፋል ወዘተ...” እንላለን፡፡

አንድ ቀላል እዉነት አለ...በየትኛዉም እድሜ ላይ ብንሆን ሁሉን ነገር ማቅለል አይደለም ማሰብ እራሱ ይከብደናል፡፡

‘ይሄ ከተከናወነልኝ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብለን መስፈርት ከሰጠን ደስተኛ የመሆን እድላችን ከጊዜ ወደጊዜ እየጠበበ ይሄዳል! ዛሬን፡ አሁን፡ እቺን ሰአት ባለን ነገር ደስታ እንፍጠርበት፡፡

ነገ እቅዶቻችን ሁሉ ቢሳኩ እንኳን ልክ ለመደሰት እቅድ ስንነድፍ ሌላ ሃሳብ፣ ሌላ ማነቆ፣ ሌላ ችግር እንፈጥራለን፡፡

ስለዚህ ዛሬን በጭንቀት ከመኖር የምንችለዉን በማድረግ፣ ከአቅማችን በላይ የሆነዉን ደግሞ ይለፍ ብለን በማሳለፍ ለራሳችን ዋጋ መስጠት!

ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ
@therapist_100
@therapist_group
ሼር @love_therapist ሼር