ቀንህ ነው አንድ ጊዜ የሞት መልአክ ወደ አንድ ሰው ጋር ይመጣና ❝ ዛሬ ያንተ ተራ ነው ልወስድህ መጥቻለሁ❞ ይለዋል ። ሰውዬውም ተደናግጦ ❝ ግን እኮ አልተዘጋጀሁም ❞ ብሎ ይመልስለታል። የሞት መልአከከም ❝ እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም የተሰጠኝ የስም ዝርዝሩ ላይ ያለው የመጀመሪያ ስም ያንተ ነው ተራህ ደርሷል ❞ ይለዋል ። ሰውዬውም ተስፍ በመቁረጥ ❝ እሺ በቃ ትንሽ አረፍ በል የሚበላ ነገር ላምጣልክ እኔም ቤተሰቦቼን እና ጕደኞቼን ልሰናበት ከዛ ይዘከኝ ትሄዳለክ❞ ይለዋል ። መልእኩም በሰውዬው ሀሳብ ተሰማምቶ ቁጭ አለ። ሰውዬው አንድ ሀሳብ መጣለት ፣ ምግቡ ውስጥ የእንቅልፍ መድሀኒት ጨምሮ ለመልዓኩ ሰጠው ። መልእክተኛው ምግቡን በልቶ ከጨረሰ በኃላ ወዲያው ቅልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው ። ሰውዬው በፍጥነት የያዘውን ስም ዝርዝር አንስቶ የራሱን ስም ከመጀመሪያው አጥፍቶ መጨረሻ ላይ አደረገው ። መልአኩም ከእንቅልፉ ሲነቃ ሰውየውን ላደረገለት መስተንግዶ ከልቡ አመስግኖ እንዲህ አለው ❝ በል እንግዲህ ወዳጄ ስላደረክልኝ እንክብካቤ ሁሉ በጣም አመስግናለው በጥሩ ሁኔታ ሰላስተናገድከኝ ለዛሬ ከመጨረሻው እጀምራለው ❞ ። ለአስተያየት እና ለማንኛውም ጥያቄ @therapist_100 @therapist_group ሼር @love_therapist ሼር ማንም ሰው ከቀኑ አያልፍም!! 2.3K views08:46