#_ጠላት_ሁል_ጊዜ_ስለ_አለፈዉ_ታሪክህ_ይናገራል_ምክንያቱም እሱ የሚያውቀው ያለፈውን ብቻ ነው። እሱ አምላክ አይደለም። የወደፊትህን አያውቀውም። #_ወደኋላ_ማሰብ_ወደኋላ ይጎትታል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን የሚናገር፤ #_ምክሩም_የምትፀና_ፈቃዱንም ሁሉ የሚፈጽም አምላክ ነው። የህይወትህ ታሪክ በእግዚአብሔር እጅ መዳፍ ውስጥ እንዳለ ካወክ እና ካመንክ ደስ ይበልህ። #_ፍፃሜህን_ያየልህ_ጌታ_የታመነ ነው። ኤርምያስ 29:11 #_ለእናንተ_ያለኝን_ዕቅድ_እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። ኢዮብ 14:5 #_የሰው_ዕድሜ_አስቀድሞ የተወሰነ ነው፣ የወራቱንም ብዛት #_ወስነህ_አስቀምጠሃል ፤ ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት። መዝሙረ ዳዊት 139 3 ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥ 4 የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ። 5 አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ። from Nardos A Yauney ይ ላ ሉን always @Live_byFaith @Live_byFaith @Live_byFaith 134 views05:02