Get Mystery Box with random crypto!

መኖር አይደለም ወይ? * * * * * | ከጥበብ እልፍኝ

መኖር አይደለም ወይ?
* * * * * *
ህያውነት እምቢ ልሁን የሙት ወዳጅ
የት ደርሶ ያውቅና? ትንሳኤን አሳዳጅ::
እምቢ ባይ ትንሳኤ
አርፎ መተኛት ነው ሙት የለው ጉባኤ::
ኗሪ ነው ጣጠኛ
አንዴ በጉባኤ
አንዴ በሱባኤ
የሚጨቀጭቀው የገዛ ናላውን
ቢጠየቅ ላይመለስ ትናንት የበላውን፡፡
ኗሪ ነው ጣጠኛ
አንዴ በዕምነቱ
አንዴ በእውነቱ
አንዴ በዕውቀቱ
እየቀባጠረ ስሌት መሳይ ተረት
ሞቱን ይራገማል የሽረት የወረት፡፡
በትርጉም በቃላት መኖር ከሚጠብህ
ሞት እንኳ በገባህ ትንሳኤው ቀርቶብህ::
ሞትህን ነው ማጥበቅ ደጉን ወዳጅህን
ማሳመርስ ጠርጎ መቃብር ደጅህን
እሱ ጋር ጽናበት
መቃብርም መቅደስ ነው መኖር ለቻለበት፡፡
እንዲያው ላመል እንጂ ሞት የምንፈራ
መኖር አይደለም ወይ? የሰው ልጅ መከራ...


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam