Get Mystery Box with random crypto!

ኤልያስ ሽታኹን * * * * * * እኔ በፀ | ከጥበብ እልፍኝ

ኤልያስ ሽታኹን
* * * * * *
እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam