Get Mystery Box with random crypto!

ትንሳኤሽ ናፍቆናል ንጋት ነበር ጥንቱን ያኔ በዚያ ዘመን ዘመን ዘመን ወልዶ ክፋት ተንኮል ሳይገን | ከጥበብ እልፍኝ

ትንሳኤሽ ናፍቆናል

ንጋት ነበር ጥንቱን ያኔ በዚያ ዘመን
ዘመን ዘመን ወልዶ ክፋት ተንኮል ሳይገን
ንጋት ነበር ጥንቱን በዚያ ዘመን ያኔ
ሳይጠናወት የጎጥ መንፈስ ጠኔ

ያኔ ንጋት ነበር
በጦቢያ ምድር
ፍፁም ድንቅ ፍቅር
የአብሮነት ህብር
እውነት የቀመረው ስውር ድንቅ ሚሲጢር።

ንጋት ነበረች ጦብያ .....

የብርሃኗ ፀዳል ለአለም የምያበራ
ለአፍሪቃ ትምክት ስሟ የምፈራ
ለዜጎቿ ደጀን ግብሯ የምያኮራ።

ንጋት ነበር ያኔ
ጎዳውሙሉ ነው ማጀቷ አልገደለም
ወተት ይፈልቀዋል ወንዟ አልነጠፈም።

ከፍ ካለው ሰማይ ደመናው ያጎራል
ወቅቱ ሳይዛነፍ ዝናሙ ይዘንባል
አይሰስትም ከቶ ምድሯ እህል ያበቅላል።

ፍቅር ነበር ያኔ

ከአማራ ምድር ላይ ጤፍ እየታጨደ
ከደቡቡ መንደር ሰንጋ እየታረደ
ገብሱ ከኦሮሚያ ለጥማችን ማርኪያ
ቅመሙ ከትግረይ ለጥፍጠት መለኪያ

አፋር ቤንሻንጉል ጋምቤላ ሱማሌ ፍቅር እያዜሙ
ሐረር እና ድሬ ከውቢት ሸገር ጋር አብሮ አየተመሙ

አንድ ኢትዮጲያ ብለን የፍቅር ገበታ በአንድ ተቆድሰናል
በሀገር ፍቅር ወኔ ጠላት መክተናል



ያኔ

እውነት አደራጀን
ፍቅር አወዳጀን
አብሮነቱ ዋጀን

ግና ዛሬ

ጥላቻ ፈረጀን
ጎጠኝነት ፈጀን
አለቅን ገረጀን።


የሀገር ፍቅር ወኔ የታለ የጥንቱ
ጠላት ሚያርበደብድ የትገባ ህብረቱ

ስለምን

በፍቅር ያዜምነው ቅኝቱ ፈረሰ
በህዝብ ህሊና ውስጥ ክፋት ተፀነሰ



በሰውነታችን ልክ እሾህ አሜኬላ ስለምን ፀደቀ
ያቆምነው መሰረት እንዴት ባለ ታምር ወደቀ ደቀቀ



ጦቢያዬ ትንሳኤሽ ናፍቆናል ነፍስ ዘርተሽ በኛ
ከፍ በይ ከፍ ይበል ሰንደቅሽ ሰንንደቅሽ ዳግመኛ

ትንሳኤሽ ናፍቆናል የቀደመው ክብርሽ
ብቅ በይ በምስራቅ ኢትዮጲያ ወዴት ነሽ።


ልዑል



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam