Get Mystery Box with random crypto!

አንቺን ሚያስጨንቅሽ ፣ የኔ ፎቶ ማብዛት እኔ ምጨነቀው ካሜራዬን ሽጬ ፣ ጠብመንጃ ለመግዛት ።። | ከጥበብ እልፍኝ

አንቺን ሚያስጨንቅሽ ፣ የኔ ፎቶ ማብዛት
እኔ ምጨነቀው
ካሜራዬን ሽጬ ፣ ጠብመንጃ ለመግዛት
።።።
አንቺን የሚገርምሽ ፣ የኔ ግምባር መውጣት
እኔን የሚገርመኝ
ሊጥ ለመስረቅ ታግሎ ፣ የሚሞት እልፍ ወጣት
።።።
አንቺ የምትዪኝ
ያንተ አዲስ አበባ ፣ ከእጄ ላይ ወድቋል
እጅህን ቶሎ ስጥ ፣ ጦርነቱ አልቋል
እኔ የምነግርሽ
እጅሽን አልሻም ፣ በሊጥ ተጨማልቋል
ሸገር ስትናፍቅሽ ፣ መቀሌሽ ርቋል
።።።።
ባፍሽ የምትነግሪኝ
ሁሉንም ሀይማኖት ፣ እንደምትወጂ
በተግባር የማይሽ
መስጅድ ቤተስኪያን ውስጥ ፣ ነው ስትፀዳጂ።
።።።
አንቺ ምትነግሪኝ
ጌታ ፈጣሪሽን ፣ እንደምትፈሪ
እኔ ግን የማውቅሽ
መኖክሴ አይቀርሽም ፣ በቡድን ስትደፍሪ
።።
ታዲያ እኔና አንቺ ፣በምን እንግባባ
ያንቺ ናፍቆት መሳቅ ፣ የኔ እውነት እምባ
እኔ ምልሽ ዘራፍ ፣ የምትይኝ እምበር
ትግልሽ እኔን ማፍረስ ፣ ትግሌ አንቺን ለመቅበር
የኔ ተስፋ አንድነት ፣ያንቺ ተስፋ አንድ ቀን
ቋንቋ እንዴት ያግባባን ፣ ኑሮ እያራራቀን?!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam