Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና አልሸፈን ያለው የጠበቃ ቃሲም ታጁዲን ነውር ክቡር የሆነውን የእስልምና ምክር ቤት ያ | Bilal Media & Communication

ሰበር ዜና

አልሸፈን ያለው የጠበቃ ቃሲም ታጁዲን ነውር

ክቡር የሆነውን የእስልምና ምክር ቤት ያረከሰውን ቃሲም ታጁዲንን የተመለከተ አስደንጋጭ መረጃ ደርሶናል። ግለሰቡ የሐጅ ብር አስመልሳለሁ በሚል በሴቶች እህቶች ላይ ምን አይነት አስነዋሪ ድርጊት እንደሚፈፅም ተመልከቱት። ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ሴቶችን መጎንተልና ማታለል ብሎም ሴክሹዋል ሐራስመንት እስከ ማድረግ የደረሰ ብልግናውን በራሱ አንደበት ስሙት።

የግል ተበዳይ በርካታ ሴቶች እንዳሉ ደርሶናል። መረጃዎችን እየሰበሰብን ነው። የግል ተበዳዪችም እፍረታቸውን ተወት አድርገው ወደ ህግ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። እንዲህ ያሉ ጋጠወጥ ቦዘኔ ግለሰቦችን ከዚህ በኃላ በአደባባይ በህግ ፊት መጋፈጥ ይኖርብናል። እነዚህ እህቶቻችን የህግ ባለሙያ ድጋፍም ያስፈልጋቸዋል።

ለማስረጃ ያህል ብቻ የአንዲትን እህት ድምፅ ከስር ለቀነዋል። ግለሰቡ ከጥፋቱ ባለመታቀቡና በድብቅ ብዙ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር "ሸይኽ ነኝ" በሚል ሽፋን ኡማውን እያታለለ በመሆኑ የግድ ጉዳዩ ግልፅ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በሀጅ ስም የሚፈፀም ነውር መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል።

መንግስት እንደነ ቃሲም ታጁዲን ያሉ ሰዎችን ህግና ስርአትን እንዲሁም ተቋማዊ አሰራርን ጥሰው ሲሄዱ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ በቸልተኝነት ዝም በማለቱ ምክንያት ስልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመው እህቶቻችን ላይ ወሲባዊ ጉንተላ ማድረግ ደረጃ ሊደርሱ ችለዋል።

ሰምታቹ አሰራጩት