2022-05-04 17:45:17
ሊቨርፑል ከ2-0 መመራት ተነስቶ 3-2 በማሸነፍ ለቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ በቅቷል። አዝናኝ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ቪያሪያል እንዴት 2-0 መምራት ቻለ? ሊቨርፑልስ ከዕረፍት መልስ ያንሰራራበት ምክንያት ምንድነው? ተከታዩ ታክቲካዊ ትንተና መልሶች አሉት።
......................................
የኡናይ ኤምሪ ቡድን ከአንፊልዱ ግጥሚያ ፍፁም የተለየ የጨዋታ አቀራረብን ይዞ መጥቷል። በመጀመሪያው አጋማሽ ቢጫ ለባሾቹ ፍጹም የተሻሉ ነበሩ። ለዚህም ቁልፉ ደግሞ የፕሬሲንግ መንገዳቸው ነበር። ከፍ ባለ ኢንቴንሲቲ ተጫውተዋል።
በአንፊልዱ ጨዋታ ወደራሳቸው ግብ ክልል ቀርበው ጥቅጥቅ ብለው ሲከላከሉ የነበሩት ቪያሪያሎች በዚህ ጨዋታ ግን በተቃራኒው ተጋጣሚያቸውን በላይኛው የሜዳ ክፍል ፕሬስ አድርገዋል።
ቪያሪያል የሊቨርፑል ተጫዋቾችን ጊዜ እና ቦታ ያሳጡ ሲሆን በአንድ ለአንድ ፍልሚያዎች እና ሁለተኛ ኳስችን በማሸነፍም ረገድም የስፔኑ ቡድን የበላይነትን ወስዷል።
የኤምሪ ቡድን 'ሰው ተኮር' (Man- oriented) የመከላከል ዘዴን ተጠቅሟል። በዚህም እያንዳንዱ ተጫዋች አንድ የተቃራኒን ተጫዋች በቅርበት ሲከታተል ነበር። ቀልብ የሚስበው ደግሞ የመሀል ተከላካዩ ፓው ቶሬስ በዚህ ሃይ ፕሬሲንግ ወቅት አማካዩ ኬይታን ከመስመሩ ወጥቶ ወደፊት በመጠጋት ማርክ አድርጓል። በዚህም ምክንያት ሊቨርፑል አላስፈላጊ ረጃጅም ኳሶች እንዲጫወት በመገደዱ በወጥነት የኳስ ቁጥጥር ሊኖረው አልቻለም።
በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለው ቪያሪያል 2-0 ለመምራት በቃ። ሁለቱም ጎሎች ከመቆጠራቸው በፊት በርካታ ተጫዋቾች የሊቨርፑል ሳጥን ውስጥ ገብተዋል።
ክሎፕ በሁለተኛው አጋማሽ ዲያጎ ጆታን በሉዊዝ ዲያዝ ቀየሩ። በዚህ ሳዲዮ ማኔ የፊት አጥቂነትን ሚና ሲይዝ ዲያዝ ከግራ ክንፍ እየተነሳ ተጫውቷል።
ቪያሪያሎች ሁልጊዜም በከፍተኛ ኢንቴንሲቲ የሚጫወተው ሊቨርፑልን ለ90 ደቂቃ በእኩል መፋለም አልቻሉም። "ነዳጅ" ጨረሱ። ተበታተኑ። ፕሬስ የማድረግ ፍላጎት ቢኖራቸውም አቅም አጡ። ደቂቃዎች በገፉ ቁጥር በአካላዊ ስራቸው ወረዱ። ሰፋፊ ክፍተቶችንም መስጠት ጀመሩ። የክሎፕ ተጫዋቾችም ተጠቀሙበት።
በሁለተኛው አጋማሽ በተሻለ መልኩ የእንግሊዙ ቡድን በተረጋጋ መንገድ ኳሱን ተቆጣጥሮ በመጫወት ቀዳዳዎችን አግኝቷል። የፊት መስመር ተጫዋቾችም ወደ መሐል በመግባት ተጨማሪ የማቀበል አማራጭ መሆን ቻሉ።
ሁለቱም ፉልባኮች ወደፊት በመጠጋት የውጪኛውን ኮሪደር ተጠቀሙበት። ሶስት ጎሎችን አስቆጥረውም የስፔኑን ቡድን አፈራረሱት።
መንሱር አብዱል ቀኒ
@lfansofliverpool
@lfansofliverpool
687 viewsAbdu11 Liverpool Salah, edited 14:45