Get Mystery Box with random crypto!

ተጋፈጪው!! በብዙ ፈተናዎችና መከራዎች ማለፍ የማይቀር አ | 👏 ልባም ሴቶች 👏

ተጋፈጪው!!



በብዙ ፈተናዎችና መከራዎች ማለፍ የማይቀር አስቀድሞ የሰው ልጅ በጥፋቱ ወደ ራሱ የሳበው ነው ታዲያ ዛሬ በመከራ በማለፋችሁ "ለምን " ብላችሁ ወደ እግዚያብሄር ዞራችሁ እንድታጉረመርሙ ሊያደርጋችሁ አይገባም ማንም ሰው ከአቅሙ በላይ የሆነ ሸክም የማያልፈውም ፈተና አልተሸከመምና ሰው እስከሆንን በፈተናና በብዙ የህይወት ገጠመኝ መከራ ማለፋችን የማይቀር ነው

ፈተናዎችሽን ተጋፈጪ አትሽሺያቸው የማይሸነፉ መከራዎች የሉምና ወዮ በቃ አበቃልኝ ፣ አቃተኝ ብለሽ ተስፋ እንዳትቆርጪ ዛሬ ላይ የከበቡሽ የህይወት ፈተናዎች ደፍረሽ ብትጋፈጪያቸው የማይሸነፉ ሆነው ነው ምን ጊዜም ማጉረምረምን በህይወትሽ ተቀዳሚ አታድርጊ ተስፋ መቁረጥንም አታንግሺ ልብ በይ

"ላያልፍ የመጣ ፈተና ላይሸነፍ የከበበሽ መከራ የለም "

ከችግሮችሽ አትሽሺ ተጋፈጪያቸው ደግሞም ታጋሽ ልብ ይኑርሽ እንዴት ቆይ ግን የእውነት መከራዎቼ ይሸነፋሉ ብጋፈጥ የምትይ አዎን ልብ በይ

ተጋፍጣ ፈተናዎቿን የምታሸንፍ ሴት የፀሎት ሴት የሆነች የእምነት ሴት የሆነች ናት ይህች ሴት የፀሎትና የእምነት ሴት ከሆነች እንዴት ተስፋ በመቁረጥ ህይወቷ ሊያበቃ ይችላል በፍፁም እንጂ የሚያበረታት ሃይልና አቅምን ብሎም እንዴት ማለፍ እንዳለባት "ጥበብን " የሚያጎናፅፋት እግዚያብሄር አለና

ምቹ ነገር ወይም በምቾት ህይወት ማለፍን ሁሌ አትጠብቂ ከምቾት ህይወት ወተሽ በመከራ አንድ እንደምታልፊ እወቂ የምትሰሪውም "ነገዋን አንቺ " የምታይውም በዚህ ውስጥ ነውና በፍፁም አታጉረምርሚ ልብ በይ "ላያልፍ የመጣ መከራ የለም" ስለዚህ ፅኚ የፀሎትና የእምነት ሴት ሁኚ ከእግዚያብሄር ጋር ያለሽ ህብረት ይጠንክር ያኔ ተጋፍጠሽ ማለፍ አይከብድሽም

አንቺ ሴት በርቺ ሁሉ ይታለፋልና ፅኚ

ከወንድማችሁ ቦና

ለአስተያየት @onlyforjesus1

Share @lebamsetoch