Get Mystery Box with random crypto!

ማንም ሳያነበው እንዳያልፍ ይማሩበታል ይፀፀቱበታል ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል ክፍል አ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

ማንም ሳያነበው እንዳያልፍ
ይማሩበታል ይፀፀቱበታል

ከጀናዛ ማጠቢያ ክፍል

ክፍል አንድ

ከለሊቱ ስምንት ሰአት አካባቢ የቤቴ በር በሀይል ተንኳኳ ። ከእንቅልፌ ባንኜ ተነሳሁ ። በቀስታ ወደ በሩ ተጠጋሁና ከፈትኩ ። በር ላይ አንድ ወጣት ቆሟል አጎቱ ነበር የሞቱት። ቶሎ መቀበር እንዳለበት ሀኪም ስለነገራቸው ተያይዘን ወደ ቤት አመራን።
........ጀናዛውን ማጠብ ጀመርኩ በመሀል ግን የሚያስደነግጥ ሁኔታ ተፈጠረ የሰውነት ከለሩ መቀያየር ጀመረ። ፊቱ ጠቆረ አካሉ ከሰለ ። እንደምንም አጥበን ጨረስን። ወደመቃብር ስፍራም ይዘነው ሄድን ። የተቆፈረው ቀብር ውስጥ ገባሁ መሬቱን ጠራረኩና አፀዳሁት የለህዱንም ስፋት ሞከርኩት። ወደ ውስጥ ጀናዛውን አስገባነው ምድር ሰውነቱን እንደነካው ከመሬት ስር ትልቅ ትል ወጣና ሰውነቱ ላይ ተለጠፈ አስወገድኩት ሆኖም ግን ሌላ ከመጀመርያው የተለቀ እባብ የመሰለ ትል ሰውነቱ ላይ ተጠመጠመ ።
ነገሩ ከአቅማችን በላይ ሆነና ትተነው ከቀብር ወጣን ።
⁽⁽ ሰላትን ወቅቱን ጠብቆ እንደማይሰግድ ከአንድ ዘመዱ ተነገረኝ

ክፍል ሁለት

ይ ቀ ጥ ላ ል

{{ሙሰልሰል ስትመለከቱ ሰላት የሚያመልጣችሁ፣}}

ኳስ እየተጫወታችሁ ሰላት የሚያልፋችሁ ሰዎች ሆይ !!!

<<ስሙ>>

ይህን አይነት አሟሟት ነው የምትሹት?

{በአላህ እምላለሁ ባጠፋሀቸው ጊዜያት የምትቆጭበት ቀን ይመጣል ።}

<<ዱንያን ለቀህ ከመውጣትህ በፊት ለኸይር ነገር ተቻኮል>>

<<ለወዳጅ ዘመድዎ ሼርና ፎርዋርድ በማድረግ ያዳርሱ>>