Get Mystery Box with random crypto!

አሁንም ወደነሱ እየሄድክ እኮ ነው... አንድ አስተማሪ ወደ አንድ የሚያስተምርበት ቦታ እየተጓዘ | 🌸🌸ከሰለፍዮች ጎራ🌸🌸

አሁንም ወደነሱ እየሄድክ እኮ ነው...

አንድ አስተማሪ ወደ አንድ የሚያስተምርበት ቦታ እየተጓዘ ሳለ መኪና ውስጥ ስለነቢዩ صلى الله عليه وسلم
ሲራ የተከፈተ የድምጽ ት/ት እያደመጠ ነበረና ስለ አንዱ ከባድ የጂሃድ ጉዟቸውና ሰሓባዎችም ስለሰሩት ጀብድ በሰማ ጊዜ ናፍቆቱ ጨመረና "እንደው ከነሱ ጋ በነበርኩና ተሳትፌ በሆነ!" ሲል አብራው የነበረችው ባለቤቱ "ከነሱ ጋር እኮ ነህ!፤ አሁንም ወደዛ እየሄድክ እኮ ነው። በዚህ ዘመን ሱናቸውን መከተልና ለሰዎችም ማስተማር በዛን ዘመን ተገኝቶ ከመሳተፍ የበለጥ አጅር የለውም እንዴ?!" ብላ ስራውን እንዲናፍቅ፣ መንገዱም ላይ ጸንቶ ከነቢዩ صلى الله عليه وسلم
ኣኺራህ ላይ ለመገናኘት ይበልጥ እንዲጓጓ አደረገችው።

እንዲህ ዓይነት እንስቶችን አላህ ያብዛልን፣ የነቢዩን صلى الله عليه وسلم
ሱንናህ አውቀው በዚህ ከባድ ዘመን ላይ ሱናቸው ላይ ከሚጸኑትና ሌሎችንም በቃልም በተግባርም ከሚጣሩት ያድርገን።
አቡዳውድ፣ቲርሚዚና ሌሎችም በዘገቡት ሐዲሥ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
ለሰሓቦቻቸው رضي الله عنهم
"ከኋላችሁ (ኣኺር ዘመን ላይ) ትዕግስት እንጂ የማያዋጣባቸው ቀናቶች አሉ፤ መታገስና ዲኑ ላይ መጽናት ፍምን ጨብጦ መያዝ ላይ የመታገስን ያክል የሚከብድባቸው ቀናቶች ናቸው። የዛኔ የሚጸና ከናንተ የሀምሳ ሰው ምንዳ ያገኛል" ብለዋል።
ሱነን-አቢ ዳውድ 4341፣ ቲርሚዚ 3058።
አላህ ጀነት ላይ የውዱን ነቢያችን ጉርብትና ያድለን። -ኣሚን-

"اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ".
@ዛዱል-መዓድ
24/6/1443ዓ.ሂ

እህቴ ሂጃብሽ ሱትራሽ ነው ሱትራሽ ደግሞ ለዱንያሽ ብቻ አይደለም ለአኼራሽም ጭምር ነው እህቴ ሆይ ተሸፈኚ በሂጃብሽም ዳግም ንግስት ሁኚ
ዛሬም ኡሙ ሀኒፍ ቢንት ሚፍታህ ነኝ

https://t.me/kukusal
https://t.me/kukusal
https://t.me/kukusal