Get Mystery Box with random crypto!

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ እህት ወንድሞቼ እንደምን አላችሁልኝ ?? ኡሙ | 🌸🌸ከሰለፍዮች ጎራ🌸🌸

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ እህት ወንድሞቼ እንደምን አላችሁልኝ ??
ኡሙ ሀኒፍ እህታችሁ ነኝ እንደጠፋሁ ይታወቀኛል በውስጥ መስመርም ሀሳብ አስተያየታችሁን ለምታደርሱልኝ በጣም ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

ዛሬ ትንሽ እንድናወራ ያሰብኩበት አርእስት የሚሆነው ያ የተከበረውና ተወዳጁ ተፈቃሪ መተዛዘኛው ያ የራህመት...የሆነው ረመዳን አለቀብን አይደል....
ምባልባት በዚህ ታላቅ ወር ተጠቅማችሁበት ከሆነ ማሻአላህ አላህ ምንዳውን በአኼራ ይክፈላችሁ ግን በዝምታ ላለፋችሁ ታላቅ ክስረትን ከስራችሁዋልና ነፍሳችንን እንክሰሳት ።
ምን ልላችሁ መሰላችሁማ እህት ወንድሞቼ ከረመዳን በሁዋላ ያለው ሀላችን ሁናቴያችን እንዴት እየሄደልን ነው ረመዳን ላይ በነበርንበት በዛው ፆማችን ስግደታችን ከሀያሉ ጌታችን ጋር መቀራረባችን እንዳለ ነው ወይስ ተቀይሯል
አደራችሁን እህት ወንድሞቼ ኡስታዛ ምን አለችን መሰላችሁ ረመዳን መጥቶ or አጊንቶ አንድ ሙእሚን የተጠቀመበት እንደሁ ከረመዳን በኃላም ትልቅ ሽልማት አለው ሱብሀነላህ ጌታችንን መታዘዛችን በራሱ በሽልማት ሲያንበሻብሸን አስባችሁታል ግን.....
ሽልማቱ ምንድነው ብለን ስንጠይቃትም ረመዷን ላይ በነበረበት አላህን መገዛት ቅንጣትም ሚያደናቅፈው ሚረታው ሳይኖር ነፍስያው ያለአንዳች ማወላወል ሳትሸነግለው ባርያነቱን ሳይዘነጋ ከጌታው ጋር በደንብ ይቀራረባል። እንዴት ያለ ትልቅ ሽልማት ነው በረበል አለሚን በዱንያ ላይ እያለህ ቅንጣት ሳያወላውል መቅጣት እየቻለ የሚምርህ ጌታህን ማምለክ.....

ያአላህ ነፍሳችንን አደራ አንተ መሀሪ ጌታ ነህና።
እናም እህት ወንድሞቼ ላስታውሳችሁ ሽቼ ነውና አደራችሁ እራሳችንን እንፈትሽ እላለሁ ወሰላሙ አለይኩም ለአላህ ብዬ እወዳችሁዋለሁ

መልእክቶችን ሼር በማድረግ ለሌሎችም ተጠቃሚ እናድርግ
አማና ኣይተን አንለፍ ሼር እናድርግ እናስታውስ
join and share
https://t.me/kukusal
https://t.me/kukusal
https://t.me/kukusal