Get Mystery Box with random crypto!

@ቁም ነገር ...ከ....jone

የቴሌግራም ቻናል አርማ kumenegerrr — @ቁም ነገር  ...ከ....jone
የቴሌግራም ቻናል አርማ kumenegerrr — @ቁም ነገር  ...ከ....jone
የሰርጥ አድራሻ: @kumenegerrr
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 317
የሰርጥ መግለጫ

@ፀሐይ ሳትኖር ሲቀር ነው እሚመሸው...ፀሐይ ካለች አይመሽም...ምሽትም ፀሐይም ፊት አቅም የለውም...የፀሐይን መሄድን ጠብቆ ነው ምሽት የሚነግሰው...በህይወታችንም ፀሐይና ምሽት አሉ...ቀለል ለማረግም ቀን እና ማታ ብለን ልንላቸው አንችላለን ...በማንም ህይወትም ውስጥ ሁሌ ቀን የለም ማታም እንደዛው.........

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-20 17:50:13 "የ አንተ እውነት የ አንተ ብቻ ነው…የ አንተን እውነት ሊሎች እውነት ነው ብለው እንዲቀበሉ አትጠብቅ።"
@kumenegerrr
28 viewsJhon, 14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:58 በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን

«በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሃል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሃል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሃል። ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"

አንድ ነገር ልንገራችሁ … በሕይወት ማንንም አትውቀሱ፡፡ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጧችኋል። መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኗችኋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኗችኋል። ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኗችኋል።


@kumenegerrr
@kumenegerrr
28 viewsJhon, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:58 በህይወታችን ሁሌም መሄድ አለብን የምንሄደው ለመድረስ ነው ቆሞ መጠበቅ አንዳንዴ ጥሩ አደለም መሄድ አለብን አሁን የምንኖረው የሀጥያት ከሆነ ወደ ንሰሀ መሮጥ አለብን የምንኖረው ህይወት የውሸት ከሆነ ወደ እውነት መሮጥ አለብን እየሄድን በርግጥ ደሰታ ላይኖር ይችላል ደሰታ ያለው ስንደርስ ነው ስንደርስ ሁሉም ነገር ያምራል።

@kumenegerrr
27 viewsJhon, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:58 አደል?
ብዙ ጥያቄዎች መልስ የላቸውም አደል? ታዲያ ብዙ ሰዎች ለምን መጠየቅን ይወዳሉ?

እግዛብሔር የነገ ሰው ይበለን
@kumenegerrr
25 viewsJhon, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:19:58 ሕይወት_ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
1. ሆስፒታል
2. እስር ቤት
3. መቃበር
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
በመቃብር ውስጥ ሕይወት ምንም ዋጋ እንደሌለው ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው። ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ ሁን። ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!
27 viewsJhon, 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:03:27 ከውድቀት ይልቅ ህልምህን እይ

መውደቅ እና መነሳት መራመድ ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ ከኛ ጋር የሚኖሩ የህይወታችን አካል ናቸው፡፡ ሁሉም ሰው ወድቆ፣ ተሸንፎ፣አቅም አጥቶ እና ዝሎ ያውቃል፡፡ህይወት የመውደቅ እና የመነሳት ጉዞ ናት፡፡ እንወድቃለን ደግሞም ከውድቀታችን ተነስተን እንሄዳለን፡፡

ህልመኛ ሰው ወደ ህልሙ ለመድረስ በሚያደርገው ጉዞ በተደጋጋሚ ይወድቃል፡፡ ይህ ሰው ሲወድቅ ከመውደቁ ካልተማረ እና ከውድቀቱ ካልተነሳ ያለመውን አያገኝም፡፡ ውድቀት መማሪያና ማደጊያ ነው፡፡ ይህ ግን እውነት የሚሆነው ህልሙን ለሚያይ ነው እንጂ ለማያይ አይደምለም፡፡ ምክንያቱም ህልሙን የሚያይ አቅም አለው፡፡ ህልማችንን ባየን ቁጥር አቅም እናገኛለን፡፡ ውድቀታችንን ባየን ቁጥር ደግሞ ይባስ እንደክማለን፡፡ ስለዚህ ከውድቀታችን ተነስተን ህልማችንን እንይ፡፡


@kumenegerrr
@kumenegerrr
34 viewsJhon, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:03:27
"መከራ/ችግር አንዳንድ ሰዎችን ይሰብራቸዋል፤ አንዳንዶችን ደግሞ የዓለም ሪከርድ እንዲሰብሩ ያደርጋቸዋል"


@kumenegerrr
35 viewsJhon, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:09:35 "እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቀጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኘ ያንተ
ግራ ነዉ። 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነዉ' ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኘ። እንዳንተ
አቋቋም ያንተ እዉነት ይሆናል ። እንደኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እዉነት ይሆናል። ባንተ እዉነት
ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኘ። የቆምኩበት ሆኜ ለስህተተህ ሒሳብ እየሰራሁ
ስዳኝህ እቀሽማለሁ።"
#ከጠበኛእውነቶች መፅሐፍ የተወሰደ።
@kumenegerrr
@kumenegerrr
@kumenegerrr
48 viewsJhon, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:09:35 ህይወት ምርጫ አላት…ግን ሁሌም አደለም…አንዳንዴ ምርጫ አይኖርም…ወይ ደሞ አንድ ምርጫ ብቻ ይኖራል…አለመምረጥ መቻል ደሞ ክፉ ነው…ምን ሆነህ ነው ስትባል እንዲህ ሆኜ ማለት አለመቻል የከፋ ነው…

@kumenegerrr
@kumenegerrr
@kumenegerr.
46 viewsJhon, 08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ