Get Mystery Box with random crypto!

ጃንደረባ ማለት በሌላ የአገላለፁ ትርጉም ድንግል ማለት ነው።ይህ ማለት ህገ ጋብቻን ንቀው ወይም ት | ቀሲስ ስንታየሁ የኔአባት

ጃንደረባ ማለት በሌላ የአገላለፁ ትርጉም ድንግል ማለት ነው።ይህ ማለት ህገ ጋብቻን ንቀው ወይም ትተው ብቻቸውን በድንግልና ህይወት ለመኖር የወሰኑ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ጃንደረባነት በ3 አይነት መንገድ ሊገለፁ ይችላል።1ኛ/ ከእናታቸው መሀፀን ጀምሮ አካላዊ የስሜት ምልክት ሳይኖራቸው ጀንደረባ ሆነው የተወለዱ አሉ።2ኛ ደግሞ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ወይም በሌላ ምክንያት በሰው አካላቸው ተሰልቦ ጃንደረባ የሆኑ አሉ። 3 ኛ/ ስለ መንፈሳዊ የእግዚአብሔር መንግስት ብለው (ስለ መንግስተ ሰማያት ብለው) ራሳቸውን ጀንደረባ ያደረጉ  አሉ። ስለዚህ ጉዳይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በፈሪሳዊያን ዘንድ ስለ ጋብቻ በቀረበለት ጥያቄ መነሻነት ማግባትም ሆነ አለማግባት ወይም ጃንደረባ ሆኖ መኖር ከእግዚአብሔር ዘንድ ለተሰጣቸው መሆኑን በሰጣቸው መልስ የጃንደረባን ምስጢር ነግሮናል።(ማቴ 19፥10-11) ስለዚህ ጠያቂያችን ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ሀብት ፀጋ ምን እንደሆነ ለይቶ በማወቅና በመረዳት በፀጋው መኖር አለበት። በጋብቻ ተመስርቶ ትውልድ ማትረፍም ከእግዚአብሔር ፍቃድ የተነሳ እንጂ ሰው በራሱ አቅም ወይም ችሎታ ያመጣው ህልውና አይደለም።በሌላም በኩል አለምን ንቀው ሁሉን ትተው በዱር በገዳም እንደሚኖሩ ባህታውያን ወይም መናንያን ሳያገቡና ዘር ሳይተኩ በጃንደረባነት የሚኖሩ ፍጹማን የእግዚአብሔር ሰዎች ደግሞ የተሰጣቸው ፀጋ ዘመናቸውን ሁሉ እግዚአብሔርን ማገልገልን በነፍስም በሥጋም ለእግዚአብሔር በመገዛት ለማገልገል ከልጅና ከትዳር የበለጠ ስም ወይም ክብር ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛሉ።ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ ጃንደረባን “እነሆ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያስኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረባዎች እንዲህ ይላልና ፤ በቤቴ በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም ሰጥቻቸዋለሁ” በማለት ለጀንዳረባዎች በጋብቻና በትዳር ከሚገኘው ትውልድ በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘላለም የማይጠፋ ስም እንደሚሰጣቸው ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል (ኢሳ 56፥3-5