Get Mystery Box with random crypto!

መራር ፍተላ ሰውዬው በራሰ-በርሀነቱ ይሸማቀቅ ነበረና 'ፀጉር የሚያሳድጉ የባህል ሃኪም አሉ' ሲባ | ♡ቅን ልቦች♡

መራር ፍተላ

ሰውዬው በራሰ-በርሀነቱ ይሸማቀቅ ነበረና "ፀጉር የሚያሳድጉ የባህል ሃኪም አሉ" ሲባል ሰምቶ ብዙ መንገድ ተጉዞና ተራራውን አቋርጦ የባህል ሃኪሙ ጋ ደረሰና አነጋገራቸው፣

"እርሶን ለማግኘት ከሩቅ ቦታ ነው የመጣሁት"

"ምን ፈልገህ ነው?"

"ፀጉር ማሳደጊያ መድኃኒት እንዲሰጡኝ ነው"

"በል እሺ! ይህንን መድኃኒት በየቀኑ ውሰድ። ፀጉርህ አንተ የምትፈልገው መጠን ላይ ሲደርስልህ መድኃኒቱን አቋርጠው" ብለው ሰጡት።

ሰውዬው መድኃኒቱን ተቀብሎ እያገላበጠ ካየው በኋላ "መድኃኒቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? እርሶ ሞክረውታል እንዴ?" ብሎ ጠየቃቸው።

ባለ መድኃኒቱም ጣታቸውን ከሰውዬው ኋላ ወዳለው ተራራ እያመለከቱ እንዲህ አሉት "ያ አልፈኸው የመጣኸው ተራራ ይታይሃል? ከዚህ በፊት ለጥ ያለ ሜዳ ነበር። መድኃኒቱን ይዤ ስመጣ ግማሹ ሜዳው ላይ ፈሰሰብኝ። ከብዙ ጊዜ በኋላ ሜዳው አድጎ ተራራ አከለ። ከዚህ በላይ ምን እልሃለሁ?"

ባሻዬ..! እኔስ ብሆን ከዚህ በላይ ምን እልሃለሁ? በዚህ የጦርነትና የኑሮ ውድነት ዘመን መሪዎቻችን ኢኮኖሚያችን አደገ ብለውናል። እነሱ ኢኮኖሚያችንን ያሳደጉት እኚህ የባህል ሃኪም ጋ ሄደው ይሆን?

changed!

@kn_lboch join