Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ቀን ባልደረባቸው ዑመር ረ.ዐ. ወደ አላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ቤት መጡ። ወደ ውስጥ ሲገቡ | KIRAMI

አንድ ቀን ባልደረባቸው ዑመር ረ.ዐ. ወደ አላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ. ቤት መጡ። ወደ ውስጥ ሲገቡም ነቢዩ ከቴምር ቅጠል የተሰራ ፍራሽ ላይ ተኝተው ነበር። ደረቆቹ የቅጠሉ ጠርዞች በውዱ የነቢይ ሰውነት ላይ ሰንበሮችን አውጥቷል። በአንድ ጥግ ትንሽ ዱቄትና ውሃ አዩ። ከነዚህ ነገሮች በቀር በቤት ውስጥ ፈፅሞ አንድም ነገር የለም። በዚህ ወቅት አረቢያ በሳቸው እጅ ነበረች። ዑመር እጅግ ደነገጡ። እንባቸውንም ማቆም አልቻሉም።

የአላህ መልእክተኛም
''ዑመር ሆይ! ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉ ጠየቁት። ዑመርም (ረዐ) እንዲህ ሲሉ መለሱ

'' እንዴት አላለቅስ አንቱ የአላህ መልእክተኛ?! የሮማና ፐርሺያ ንጉሶች በምቾት ሲንደላቀቁ፣ የአላህ ነቢይ ግን ከቴምር ዛፍ ቅጠል በተሰራ ደረቅ ፍራሽ ላይ ይተኛሉ?!''

ነብዩ እንዲህ አሉ

'' ዑመር ሆይ፣ ቄሳርና የፋርስ ንጉስ በዚህ አለም ይደሰቱ! ለኛ ግን የቀጣዩ ዓለም ደስታ በቂያችን ነው! ይህ አለም ለእኔ ከቶ ምን ያደርግልኛል?! የኔና የዚህች አለም ግንኙነት እንደ በጋ መንገደኛ ነው! ከዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ መልሶ እንደሚጓዘው።''

@Nebizeyna