Get Mystery Box with random crypto!

እብዱ ደራሲ ክፍል ስድስት በመغፊራ ቢንት ፉላን ............ አረማመዳችንን ላየ ቶሎ ብለ | KIRAMI

እብዱ ደራሲ ክፍል ስድስት
በመغፊራ ቢንት ፉላን
............
አረማመዳችንን ላየ ቶሎ ብለህ ና ተብሎ በማስፈራርያ የተላከ ህፃን ነው ምንመስለው ከእርምጃ በጣም በፈጠነ ከእሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ታክሲ መያዣው ጋር ደረስን ታክሲ ሰልፉ እንደዛሬ ረዝሞብኝ አያውቅም ደሞ ለእልሁ ታክሲውም የለም የምንሰራበት ድርጅት መሀል መርካቶ እንደመሆኑ መጠን በስራ መውጫ ሰአት በጣም ብዙ ህዝብ ነው የሚኖረው ያንን ሁላ ሀልቅ ደሞ ሲኖ ካልጫነው በስተቀር አያልቅም። ደሞ ሚጋፋው ህዝብ ብዛቱ ደና ሰልፍ ይይዙ እና ልክ ታክሲ ሲመጣ ሰልፍ የለ መጋፋት ና መራገጥ! አንዳንዱማ እርግጫው አህያ ያስቀናል!የመገናኛ ታክሲ ብዙ ቢመጣም ህዝቡ ሁላ እዛ ሚሄድ ይመስል ታክሲው አይበቃም ግማሹ በቅጥቅጥ፤ግማሹ በሀይገር ቢሄድም ህዝቡ ግን ምንም ያህል ሊቀንስ አልቻለም እንደውም የጫናቸውን በጀርባ እያመጣ ሚገለብጣቸው ነበር የሚመስለው። ብቻ አሰልቺ ነው እኔ ና ሰሙ ሌላ ጊዜ አደለም ልንራገጥ እና ልንጋፋ ይቅርና ብንገፋ ራሱ ይቅርታ እንጠይቅ ነበር፡ዛሬ ግን መቆም ሁላ ሰልችቶናል ተጋፍተን እንደማይሆንልን እያወቅን መጋፋትን መርጠናል ግን ምንም ሊሳካልን አልቻለም እንደውም አንድ አህያ የሚያስንቅ ሰውዬ እግሬን ረገጠኝ በጥፊ ብለው ሁላ በጣም ደስተኛ ነበርኩ! ደሞ ከሱም ብሶ እያየሽ አትጋፊም?አለኝ ሰሙ ሳቅ መቆጣጠር የሚባል ነገር አልፈጠረባትም ሳታስበው በሰማችው የሰውየው ንግግር ሳቋን ለቀቀችው ና እኔን ከመሀል ጎትታ አወጣችኝ እኔ ለራሴ እግሬን አሞኛል አንቺ ትገለፍጫለሽ አ።?ብዬ ግልምጥ አደረኳት!እሷ ግን አደለም አይዞሽ ልትለኝ ማውራት እስኪያቅታት ትንተከተካለች አሁን ከሰውየው እርግጫ እና ግልምጫ የባሰ የሷ ሳቅ አበሸቀኝ።ችግር አለብሽ ወላሂ አንዴ መሳቅ ከጀመርሽ አታቆሚም አ?ደሞ ምን አለ ሚሳቅበትን ቦታ እንኳን በስርዐት ብታውቂ?ኡሚ እንደዛ ሆና እየጠበቀችን አንቺ እዚ ታሽካኪያለሽ? ገደል ጊቢ ስፈልጊ !ብዬ ሰሙን ጥያት ወደ ታክሲው ሰልፍ ሄድኩ የተናገርኳት ሁሉ በንዴት እና በጭንቀት ብዛት ቢሆንም ጥፋተኛ ነች ብዬ ደምድሜያለው። እሺ በቃ ይቅርታ!ነይ ራይድ እንጥራ? እኔጋ ብር ስላለ እኔ ከፍላለው አለችኝ በተሰበረ ድምፅ ምንም መልስ አልሰጠውኋትም! ሰሙን አስከፍቻታለው ግን አሁን ከሷ በላይ የማሂር ነገር ነው ሚያሳስበኝ ስለዚ መለማመጥም ይቅርታም መጠየቅም አልፈለኩም። ራይዱ በ5 ደቂቃ ውስጥ ያለንበት መጣ እቤት እስክንደርስ በጣም ቸኩያለው የኔ ፍጥነት ደሞ የተለየ ነበር ሹፌሩን ቀይሬው ብነዳ ሁላ ደስተኛ ነኝ ይህን ያህል ያንገበገበኝ ግን ምንድነው? መመለስ ያልቻልኩት ጥያቄ!የትራፊክ መብራቱ 2 ደቂቃ ሳይሆን 2ሰዐት ሆነብኝ፧ ልጅ ጥላ እንደመጣች እናት ነበር ያደረገኝ ሰሙ ግን ተረጋግታለች ፊቷ ቢረበሽም ልቧ በጭንቀት ቢወጠርም የኔን ያህል አልቸኮለችም ግን የረበሻት የኔ ንግግር ይሁን የማሂር ነገር አላወኩም ዝም እንደተባባልን ሰፈር ደረስን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወደሰፈር መግቢያ ጋር ስንደርስ ሰሙ እዚጋ አውርደን አለችው ሌላ ቀን በራይድ ስንመጣ ቤት ያድርሰን የምትል ልጅ ዛሬ ጭራሽ ሰፈር መግቢያው ላይ በቃ ተናዳለች ወደ ቤቷ ልትሄድ ነው ብዬ ስላሰብኩ ምንም ሳልል ወረድኩ እሷም ሂሳቧን ከፍላ ተከተለችኝ። ወደነሱ ሰፈር መግቢያ ቅያስ ጋር ስንሄድ ትሄዳለች ብዬ ነበር ግን እንደፈራሁት አላደረገችም ትንሽ ቅልል አለኝ።ወደ እኛ ሰፈር ስንቃረብ ሰሙ እጄን ይዛ አስቆመችኝ እና እህቴ በጣም እንደጨነቀሽ የማሂርን ነገር ለማየት እንደቸኮልሽ አውቃለው ግን መጀመርያ እራስሽን አሳምኚው ሁሉንም የሚያደርገው አላህ ነው እናም ተረጋጊ ተረብሸሽ ኡሚን እንዳትረብሻት አለችኝ ከኡሚ ጋር በስልክ ያወሩት ነገር ሰሙ ፊቷ ሲቀያየር ኡሚ የኔን ድምፅ ስትሰማ የደነገጠችው ድንጋጤ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ አሳመነኝ ሳላስበው ማሂር ሞቷል አይደል ሰሙ ብያት እንባዬ ያለ ገልጋይ መፍሰስ ጀመረ ሰሙ በጣም ደነገጠች ወላሂ ውዴ እንደዛ አደለም እኔ ምንም ማውቀው ነገር የለም የተፈጠረውን ነገር ስለማናውቅ እንጠንክር ብዬ ነው ብላ እሷም እንባዋን ያለ ከልካይ አፈሰሰችው።አሁን ስድቡም ሳቁም ተረስቶ ሁለታችንም በማሂር ሀሳብ ገብተናል ሰሙ ሁሉንም እንዳልተፈጠረ አድርጋ ትታዋለች። እንባችንን ጠራርገን ወደ ሰፈር ገባን ሰፈር ውስጥ ምንም አዲስ ነገር አላየሁም ምን አልባት ዘመድ ስለሌለው ይሆን? እቤት ስንገባ ኡሚ እቤቱን አጫጭሳ ቡና አፍልታ እየጠበቀችን ነበር ሱፍራ ላይ ሰሙ ምትወደውን የክትፎ ጥብስ በአንድ ሰሀን እኔ የምወደውን እሩዝ በአንድ ሰሀን ሻይ አድርጋ እየጠበቀችን ነው የማየውን ነገር ማመን አልቻልኩም ኡሚን የጠበኳት እያለቀሰች አዝና ምናምን ነበር ግን ከጠበኳት በተቃራኒ ነበር ያገኘውሀት እኔና ሰሙ ተያየን ብቻ የኡሚ እንደዚ መሆን ሁለታችንንም አረጋግቶናል ግቡ እንጂ ምን ይገትራቹሀል፤ እናንተን ስጠብቅ ቡናውን እኮ ቀቀልኩት አለችን ሁላታችንም ሰላም ብለናት ቦርሳችንን ጥለን እጃችንን ልንታጠብ ወደ ውስጥ ገባን ሰሙም እኔም ግራ ቢገባንም ኡሚ ስላቻኮለችን ምንም ሳንል ወደ ሳሎኑ ተመለስን በሱፍራው ዙርያ ተቀምጠን ምግብ መብላት ጀመርን ኡሚ ማሂርን ከነመፈጠሩ የረሳችው ትመስላለች እኔ እና ሰሙ ግን ማሂርን ማሰብ አላቆምንም ኡሚን መጠየቅም ፈርተናል ምን አልባት ማሂር እኛ እንደገመትነው ሆኖ ቢሆን እና ኡሚ እሱን ለመርሳት ቢሆንስ እንደዚ እያደረገች ያለችው? ኡሚ ቀኑን ሙሉ የሰራችውን ሁሉ እያወራችህን ነበር ግን አንዴም ቢሆን ስለ ማሂር አላነሳችም በጣም ግራ ገብቶኛል አሁን ግን ልጠይቃት ወስኛለው እኔ ምልሽ ኡሚ ወዬ አለችኝ በጣም እየፈራው ቢሆንም ማሂር እንዴት ሆነ? አልኳት የፈራሁት አልቀረም ኡሚ እንባዋን ያለከልካይ አወረደችው ሰሙ እና እኔ ድንጋጤ አደነዘዘን በተቀመጥንበት ደርቀን ቀረን ተነስተን እንኳ ኡሚን ለማማበል አልደፈርንም .......
ክፍል ሰባት ይቀጥላል....