Get Mystery Box with random crypto!

እብዱ ደራሲ ክፍል አምስት በመغፊራ ቢንት ፉላን ......... እኔና ሰሙ የደወለችው ኡሚ መሆኗ | KIRAMI

እብዱ ደራሲ ክፍል አምስት
በመغፊራ ቢንት ፉላን
.........
እኔና ሰሙ የደወለችው ኡሚ መሆኗን ስናውቅ በድንጋጤ ቆመን ቀረን መንገድ ላይ ስለሆነ ያለነው ስልኩን ማንሳት አልፈለኩም ኡሚ ስለ ማሂር ምንም አለችኝ ምን መንገድ ላይ ማውራቱን አልፈለኩትም ሰሙም ሀሳቤን ተገራታኛለች ኡሚ ደጋግማ ብትደውልም ቢሮ እስክንገባ ላለማንሳት ወስነናል ሌላ ቀን እያዘገመን ሚያጥርብን መንገድ ዛሬ ግን ረዝሞብናል ሁለታችንም ውስጣችን በፍርሀት ተሞልቷል እንዴትም ብለን ቢሮ ስንደርስ የቢሮውን በር ክፍት አገኘነው ሁለታችንም በድንጋጤ እና በመሰላቸት አይነት አስተያየት ተያየን በቃ ሰውዬሽ መቷል ማለት ነው አለችኝ በሹክሹክታ ይሆናል በቃ ኤጭ ካልጠፋ ቀን በዚ ሰዐት ይመጣል ምኑ ብሽቅ ነው በአላህ አልኳት ስንገባ የሚከተለንን የስራ ብዛት እያሰብኩኝ፤ አለቃችን ከእድሜ ብዙም ከኛ አይበልጥም ነገር ግን ነገረ ስራው ሁላ እንደሽማግሌ ነው መነጫነጭ በጣም ይወዳል ሰሞኑን እቃ ሊያመጣ ወደ ዱባይ ሄዶ ስለነበር ደህና ተገላግለነው ነበር ደሞ ሳይናገር ነው የሚመጣው እሱ እዚ ቢሮ አለ ማለት ማውራት የለ መሳቅ የለ ስልክ ማውራት የለ በፈለጉ ሰዐት መውጣት መግባት የለ ከእኔ ጋር ማ የሆነ ጂኒ አያይዞታል ሲሀም እንዲ ሆነ ሲሀም እንደዛ ሆነ ሲሀም በዚ ገባ ሲሀም በዚ ወጣ በደቂቃዎች ውስጥ 50ጊዜ ነው ስሜን ሚጠራው በሱ የተነሳ ስሜን ራሱ ጠልቼዋለው አንዳንዴማ እዛ ቢሮ ውስጥ ካለእኔ ሰራተኛ ያለ አይመስለውም ሰሙን ከነመፈጠሯ ረስቷቷል ሌላ ቅርንጫፍ ቢኖረውም እሱ ግን ካለዚ ቢሮ ያለው አይመስለውም አሁንማ ጭራሽ ከአጠገባችን ያለውን ቢሮ የራሱ ሊያደርገው እያሳደሰው ነው እሱ እዚ ቢሮ የገባ ቀን እኔ ወደ ሌላ ቢሮ ቀይሩኝ እላለው ወይም ከስራው እለቃለው ስላት ከትከት ብላ እየሳቀች ስለሚወድሽ ነው ኮ ትለኛለች ለዛም ነው ሰውዬሽ ምትለኝ ።እኔ ግን አሁን ከስራው እና ከአለቃችን በላይ የማሂር ነገር በጣም አሳስቦኛል ቢሮ ከገባን በውሀላ ለኡሚ መደወል እንደማልችል ብደውልም በስነስርዐት እንደማላወራት ስላወኩኝ ሰሙን ከመግባታችን በፊት እንደውልላት አልኳት ሰሙ ምንም እንኳን የማሂር ነገር ቢያስጨንቃትም ኡሚን በተጣደፈ አነጋገር ማናገሩን አልመረጠችም እሱ ለምሳ መውጣቱ ስለማይቀር በዛ ሰዐት እንደውላለን ባይሆን እንዳትጨነቅ አለቃችን እንደመጣ ንገሪያት ስራ እንደበዛብን ይገባታል ብላኝ ለኡሚ ደወልኩላት ግን ለማናገር ድፍረቱን ስላጣው ለሰሙ ሰጠውኋት ሰሙ የኡሚን ድምፅ ስትሰማ ፊቷ ተቀያየረ ግን እኔ እንድነቃባት ስላልፈለገች በግድ ለመሳቅ እየሞከረች ነበር ነገሩ ግራ ስለገባኝ ስልኩን ተቀብዬ ኡሚ ደና ነሽ አልኳት ኡሚ ድምፄን ስትሰማ እንደደነገጠች ድምጿ ያሳብቅባታል ከኡሚ ድምፅ ጀርባ ለቅሶም አይሉት ሳቅ የሚመስል ድምፅ ይሰማኛል አሁን ከቅድሙ የበለጠ ልቤ በፍርሀት ልፈነዳ ደርሳለች ደና ነኝ ሲሁ እንዴት ዋልሽልኝ እህትሽ እኮ አለቃቹ እንደመጣ ነገረችኝ ስራ ይበዛባቹሀል በቃ ጠንክሩልኝ ልጆቼ ደና ዋሉ በተመቻቹ ሰዐት ደውሉልኝ በቃ ካልሆነም ቤት ኑ አብራቹ ምትወዱትን ምሳ ሰርቼ ጠብቃቹሀለው ብላ ምንም መልስ እንዳልሰጣት በሚመስል መልኩ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችብኝ። ይሄ የኡሚ የሁልጊዜ ንግግር እንደሆነ ባውቅም የዛሬው ግን የሀዘን እና የስስት ነገር አለበት። አሁን የበለጠ ልቤ ፈርቷል ቦርሳዬ ውስጥ ባይሆን እና ይ የተመታ ሰውዬ ባይመጣ ኖሮ ወደቤት እሄድ ነበር አሁን ግን ግዴታ ነው መግባት እና ከሰሙ ጋር ወደ ውስጥ ገባን ገና ከመግባታችን እሺ ማጂላኖች በስራ ሰዐት እንኳን አትቀመጡም ብሎ በነገር ለኮሰን ምን አለ አሁን የመጣው ከዱባይ ነው ሰላምታው አይቀልም የተረገመ ሼባ ብዬ በውስጤ ተሳድቤ ወደ ቦታዬ ሄጄ ተቀመጥኩኝ ገና ከመቀመጣችን ይህን የስራ order ጀመረ በቃ እኔና ሰሙ የማሂርን ነገር ባንረሳውም ግን አሁን 75% የሚሆነው ሀሳባችን ስራው ላይ ሆኗል ሳናውቀው ሰዐቱ 9 ሆኗል ለካ አረ ዙሁር እንስገድ አለች ሰሙ በዛውም ምሳ እንብላ አይነት መልእክት በቃ በተራተራ ስገዱ ምሳ ደግሞ እኔ ነኝ ምጋብዛቹ እዚው አብረን እንብለላን ብሎ የኛን ፍቃድ እንኳ ሳይጠይቅ ደውዬ ልዘዝ ብሎ ወጣ ምሳ ሰዐት ላይ ኡሚ ጋር እንደውላለን ብለን የነበረ ቢሆንም ይሄ ሰውዬ ግን ምንም እረፍት ሊሰጠን አልቻለም ሁለታችንም በሰጨት ብለን የየራሳችንን ስድብ አወረድንበት እና በቃ ውዴ ተረጋጊ አላህ ያለው ነው ሚሆነው ብላ ግንባሬን ሳመችኝ እና ለኡዱ ወጣች በተራ በተራ ሰገድን እና ምሳችንን መቶ በልተን ወደ ስራችን ገባን አሁንም እንደቅድሙ በስራ ተወጥረን ሳናውቀው 12 ሰዐት ሆኗል ለካ ኡሚ ደወለች በድንጋጤ ቀና ብዬ ሰሙን አየውሀት አለቃችን ፊትለፊት ስለነበር ማውራት አልቻልንም ዝም ብዬ ስልኩን አንስቼ ወዬ ኡሚ አልኳት አሁን ከቅድሙ ድምጿ መረጋጋት አለው እናንተ ልጆች ቡናው ኮ ቀዘቀዘ አለችኝ መጣን መጣን ኡሚ ልንወጣ ነው አልኳት በዛውም ለሰሙ እንውጣ ለአዩብ ደግሞ ልንወጣ ነው የሚል መልእክት እያስተላለፍኩ ነው። ስልኩን ስዘጋው በቃ ሂዱ ጠዋት በጠዋት ኑ እና ትጨርሱታላቹ አለን ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነው እሺ ደና እደር ብለን ተያይዘን ውልቅ ብለን ወጣን ሁለታችንም እቤት እስክንደርስ ቸኩለናል ኡሚ ስለማሂር ምን ትለን ይሆን ማሂር ምን ሆኖ ይሆን.......?
ክፍል ስድስት ይቀጥላል ......