Get Mystery Box with random crypto!

እብዱ ደራሲ ክፍል አራት በመغፊራ ቢንት ፉላን ........ እንደገመትኩት ነበር የሆነው ከድር | KIRAMI

እብዱ ደራሲ ክፍል አራት
በመغፊራ ቢንት ፉላን
........
እንደገመትኩት ነበር የሆነው ከድርጅቱ ደውለው ፈተናውን እንዳለፍኩ እና ስራ መጀመር እንዳለበኝ ተነገረኝ። የሀዘን እና የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ፤ቀስ ብዬ ኡሚ ጋር ሄድኩ እና ነገርኳት ኡሚ በጣም ትጨነቅላታለች "በቃ አትንገርያት ይከፋታል ለሷ ካልተደወለላት ስራው ይቀራል ከፈለገ! እኔ እናታቹ እንድትለያዩብኝ አልፈልግም አሁን ሂጂ እና ቀስቅሻት ቁርስ ደርሷል"አለችኝ።ኡሚ እንደዛ ስትለኝ ቅልል አለኝ ወደ ክፍሌ ስገባ ሰሙ ነቅታለች "ሴትዬ ተነስተሻል እንዴ?ነይ በይ ቁርስ ቀርቧል" አልኳት እና ወጣው ሰሙ ፊቷ ልክ አደለም የተረበሸ ከተማ መስላለች ቁርሱንም በስነስርዐት እየበላች አደለም የሰሙን እንደዛ መሆን ስናይ የኔም የኡሚም ግምት አንድአይነት ነበር "ምነው ሰሙ ደና አይደለሽም እንዴ ፊትሽ ልክ አደለም?" አለቻት ኡሚ "አረ ምንም አልሆንኩም ኡሚ ስቃዥ ነበር ያደርኩት" አለቻት እየዋሸች እንደሆነ ሁለታችንም አውቀናል "አብሽሪ እህቴ ብዬ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት" አንገቴ ውስጥ ተወሽቃ "ወድሻለው እሺ ምንም ይሁን ምን ካንቺ አይበልጥብኝም" ስትለኝ ሳላስበው እንባዬ ወረደ ኡሚ ብቸኛ ልጇ ስለሆንኩ እንደዚች አይነት እህት በማግኘቴ በጣም ደስ ብሏታል "አብሽሩልኝ እኔ እናታቹ እያለው ማንም አይለያቹም!"ብላ ሁለታችንንም ሳመችን እና የበላንበትን እቃ አንስታ ወደ ኩሽና ገባች ሰሙም ሱፍራውን ጥቅልል አድርጋ ኡሚን ተከተለቻት ኡሚና ሰሙ በሹክሹክታ ሲያወሩ ይሰማኛል፤ ኡሚ ለሰሙ እየነገረቻት ይሁን? ብዬ በጣም ፈርቻለው። ወሬያቸውን ጨርሰው ከኩሽና ሲወጡ ኡሚ ያለመደባትን "ሂዱ በሉ የሰሙን ቤት ፏ ፏ አድርጋቹ ኑ" ብላ ላከችን "ሰሙም አይ እኔ ብቻዬን እሄዳለው" አለች? "ከመች ጀምሮ? አለች" ኡሚ በመቆጣት ድምፅ እኔም ግራበመጋባት ቀና ብዬ አየውሀት እንደከፋት በጣም ታስታውቃለች ኡሚን በቁጣ አይነት አስተያየት ሳያት"ምን ታፈጪብኛለሽ?ተነሺ ደርሳቹ ኑ" አለችኝ አሀ ሌላ ቀን የሰሙን ቤት አፅድተን እንኳን እንመለስ ስንላት የምን ቤት ነው? የሷ ቤት እዚ ነው! እንደውም እቃውን ጭናቹ ኑ! ነበር የምትለን ዛሬ ምን ተገኘና ነው? በቃ ሰሙ ፈተናውን አላለፈችም!ኡሚም ነግራታለች ለዛ ነው ሰሙም ብቻዬን እሄዳለው ያለችው።ኡፍ ኡሚ ደሞ ምን አጣደፋት ደሞ ከፈለገ ይቀራል ብላኝ አልነበር እንዴ? ብቻ በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኜ ከሰሙ ጋር ተያይዘን ወጣን። የሰሙ ቤት ከኛ ብዙም አይርቅም፤ሌላ ቀን በእግራችን ነበር ወደሷ ቤት የምንሄደው፤ ዛሬ ግን ሁለታችንም አይደለም እየተጓተትን በእግራችን የመሄድ ታክሲውም ቀርቶብን እቤት ብንቀመጥ ሁላ ደስተኞች ነበረን። ከኡሚ ጋር ላለመነታረክ ነው የወጣነው፤ምንም አላወራንም። አንዴ ብቻ ሰሙ "ሲሁ ከድርጅቱ ደወሉልሽ እንዴ? አለችኝ። በጣም ነው የደነገጥኩት "አይ አረ አልደወሉም ላንቺ ደወሉልሽ እንዴ?" አልኳት "አይ" አለችኝ ብቻ እንደዛ እንደደባበረን የሰሙን ሁለት ክፍል ቤት እንደነገሩ አፀዳድተን ያልታጠበውን እቃ አጥበን ወደቤት ተመለስን።
..........
እቤት ስንገባ ኡሚ ጓረቤት ሰብስባ ዳቦ ደፍታ ቤቱን በዐል አስመስላ ነበር የጠበቀችን።ገና ከበር ስንገባ በእልልታ ጊቢውን አቀለጠችው እኔም ሰሙም ተያየን ሁለታችንንም አቅፋን አለቀሰች ለካስ ሁለታችንም ፈተናውን አልፈን ኖሯል ደስታችን ልክ አልነበረውም ከሳምንት በውሀላ ሁለታችንም ስራችንን ጀመርን አንድ ድርጅት አንድ ቢሮ ላይ ሰሙ አንዳንዴ ቤቷ ብዙውን ጊዜ እኛ ቤት መኖር ጀምራለች።
..................
"ነይ በቃ ምግብ አልበላሁም እየሄድን እነግርሻለው" አልኳት እና የቢሮውን በር ዘግተን ወጣን። ወደ ምግብ ቤቱ ስንሄድ ጠዋት የሆነውን ከሀ እስከ ፖ ነገርኳት ሰሙ ማሂርን እኛ ቤት ስትመላለስ ታውቀዋለች የመጀመርያ ሰሞን ትፈራው ነበር አረ!ጭራሽ ወደሰፈሩ መምጣት አቁማ ነበር ከጊዜ ቡሀላ ግን ማሂር እብድ አደለም! ብላ ትሞግት ጀምራለች። በነገርኳት ነገር አዝናለች፤ የኔ ስሜት ተጋብቷባታል ፤ተፅናንታ ልታፅናናኝ ፈልጋለች:ግን ሁለታችንም ውስጣችን ፈርቷል ማሂር ሞቶ ይሆን? የሁለታችንም ጥያቄ ነው! ግን ማን ይመልስልን? ምግቡን አዘን እንደነገሩ ቀማምሰን ተውነው፤ "ምነው?ምግቡ አልጠፈጣቹም እንዴ?" የሚለው የእማማ ጥያቄ ነበር ከሀሳባችን ያባነነን፡ልክ እንደተመካከረ ሰው እኩል "አረ ይጣፍጣልእማማ!"አልን ንግግራችን ለራሳችን ፈገግ አደረገን እና ሂሳብ ከፍለን ወጣን የሁለታችንም ሀሳብ ማሂር ጋር ነበር ምንም ማውራት አልፈለግንም እናውራ ብንልስ ውስጣችን እየተረበሸ እንዴት ብለን ብቻ በሀሳብ ተጠምደን ወደ ቢሮ በዝግታ እየሄድን የኔ ስልክ ጠራ ኡሚ ነበረች.......
ክፍል አምስት ይቀጥላል.........