Get Mystery Box with random crypto!

እብዱ ደራሲ ክፍል ሁለት በመغፊራ ቢንት ፉላን .................... 'ሲሁ ሲ | KIRAMI

እብዱ ደራሲ ክፍል ሁለት
በመغፊራ ቢንት ፉላን
....................
"ሲሁ ሲሀም ተነሺ እንጂ ስራ ረፍዷል፡ እንደ ቀልድ ሱብሂ በሰዐቱ መስገድ ተውሽ አይደል? እሺ አሁን ብድግ በይ ውሀ ሳልገለብጥብሽ"ብላኝ ወደ ኩሽናዋ ሄደች በጠዋት እንቅልፍ ማልደራደረው እኔ ስልኬን ከአጠገቤ ሳብ አድርጌ ሰዐቱን አየሁት ምክንያቱም ኡሚ ሁሌ ሱብሂ ልትቀሰቅቀኝ ስትፈልግ ስራ ረፍዷል ነው ምትለኝ እንዴት እንደምበሳጭባት! አንዴ ከተነሳው እንቅልፍ ስለማይወስደኝ በተነሳው ሰዐት ነው መስገድ ምፈልገው: እሷ ግን አትሰማኝም "ሱብሂ መስገድ ቀንሽን ሙሉ ደስተኛ እንድትሆኚ ያደርግሻል" ትለኛለች ለኔ ደስታ ሚሰጠኝ የጠዋት እንቅልፍ መሆኑ አይገባትም ግን ላለመጨቃጨቅ ስል"እሺ"እላታለው ኡሚ ግን እሺ ማለቴ የባሰ ያናድዳታል። "ሁሌ እሺ ብቻ እስኪ አንድ ቀን እንኳን ተግብረሽ አሳይኝ" ትለኛለች አሁን አሁንማ ሰለቻት መሰለኝ በስራ ሰዐት ነው ምትቀሰቅሰኝ ግን ምንም ቢሆን ከ12:40 አታሳልፈኝም ነበር፤ዛሬ ግን ረፍዷል ስልኬን ሳየው 1:05 ይላል ውሀ እንደተረጨ ሰው ብርድልብሴን ወርውሬ "ኡሚ ግን ምን ሆና ነው?እስካሁን ያልቀሰቀሰችኝ" እያልኩ እየተነጫነጭኩ ሻወር ለመውሰድ ወጣው።ትላንት ስዞር ስለዋልኩ እና አምሽቼ ስለተኛው ሰውነቴ ዛል ብሏል ሻወር ስወስድ ከለቀቀኝ ብዬ ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ሻወር ወሰድኩ ግን ምንምን ስራ የመሄድ ሙዱ ሊመጣልኝ አልቻለም ግን ደሞ ግዴታ ነው!ለሰሙ አልነገርኳትም፤ ይህን እያሰብኩ ስልኬ ጠራ ሰሙ ነበረች
"እ አንቺ ጨራረሽ" አለችኝ "ምን አለ ደና አደርሽ ቢቀድም?" አልኳት "ትላንት አብረን መስሎኝ ያመሸነው በይ ነይ ውጪ እየደረስኩ ነው" ብላ ስልኩን ዘጋችብኝ "ምን አለ እንዳወራ እንኳን እድሉን ብትሰጠኝ ኡፍ ሰሙ ደሞ አሁን ደውዬ አልሄድም ብላት ራሱ ቤት መታ ለኡሚ አቃጥራ ታስወጣኛለች ከነሱጋር ከምንዛዛ ደሞ ብሄድ ይሻለኛል"ብዬ ልብሴን መልበስ ጀመርኩ "አንቺ ልጅ አረ ባክሽ ነይ ውጪ! ሻዩ ቀዘቀዘ እኮ አረ ምን ይሻልሻል በአላህ? ሰው አንድ ቀን እንኳን አያልፍለትም? ጓደኛዬ ትታዘበኛለች እንኳን አትይም እንዴ? አረ ተይ ሲሁ ቀልብ ግዢ ተይ"ኡሚ ምክሯን ልጀምር ነው። "ጨርሻለው ኮ ኡሚ ደሞ ቁርስ አልበላም፤አራበኝም" አልኳት ከክፍሌ ውስጥ ሆኜ፤ "አራበኝም ማለት ምን ማለት ነው? ከእንቅልፍሽ አደል እንዴ የተነሳሽው? ነይ ውጪ እና ቢ!"ቁጣ እና ትእዛዝ የተቀላቀለበት ድምፅ!መልስ ልሰጣት ስል የውጪው በር ተንኳኳ "ይሀው ጓደኛሽ መጣችልሽ ስትንከራፈፊ"ብላኝ በሩን ልትከፍት ወጣች "ኡፈይ አልሃምዱሊላህ ገላገልችኝ"ብዬ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ከክፍሌ ወጣው። ጫማዬን እየፈለኩ እንዳለ ኡሚ መጣች ከውሀላዋ ጓረቤታችን ወይዘሮ አኢሻ ተከትለዋት ገቡ። ፊታቸው ልክ አደለም መርዶ ነጋሪ ነበር ሚመስሉት፤ ኡሚም ተረብሻለች፤አጠገቧ እንደቆምኩ እንኳን አላስተዋለችም፤ "ደሞ ማን ሞተ አይ እኛ ሰፈር አዝራኤል አንዴ ከገባ ካልጠራረገን አይወጣም አደል?"እያልኩ እያሰብኩ ጫማዬን ለብሼ እንደጨረስኩ ሰሙ ደወለች "አረ አንቺ ሴትዬ ነይ ውጪ ያምሻል አ ሰዐት ኮ ረፍዶል ወላሂ ጥዬሽ ነው ምሄደው" ብላ ስልኩን ዘጋችው። እንደተበሳጨች ስለገባኝ ኡሚን "ደና ዋይ ብያት"ልወጣ ወደ ሳሎን ስገባ እሷም ከሳሎኑ ስትወጣ በር ላይ ተጋጨን ግን ትዝም አላልኳት! "ኡሚ ደና ዋይ በቃ ልሄድ ነው" ብዬ እንደለመድኩት ግንባሯን ልስማት ጠጋ ስል አይኖቿ እንደ ጉድ እንባን ያዘንባሉ፤በጣም ነበር የደነገጥኩት "ኡሚ ምንድነው የሆንሽው?ማነው የሞተው!ማን ምን ሆኖ ነው?" መልሷን አልጠበኩም ነበር "ምንም ምንም አደለም ልጄ ሂጂ በይ ወደ ስራሽ በጊዜ ተመለሺ የጊቢውን በር ቆልፈሽ ሱቅ አስቀምጪልኝ።" ብላ ጉንጪን ሳም አድርጋኝ ከቤት ወጣች ጨራርሼ ስለነበር ተከትያት ወጣው።"አይ የኔ ልጅ፣ የኔ የዋህ፣አይ ማሂርዬ" የሚሉ ከአንደበቷ የሚወጣ የለቅሶ ድምፅ ይሰማኛል። ጓረቤታችን እትዬ አይሻም "በልጅነቱ እንደዛ መሆኑ ሳያንስ አይይይ የሰው ልጅ መከራ እናቱ ምን ትል ይሁን አይይ ማሂር" እያሉ ከኡሚ ጋር ተከታትለው ከጊቢ ወጡ.....
ክፍል ሶስት ይቀጥላል .......