Get Mystery Box with random crypto!

እሳቸው ከመቶ አመት በፊት ገላህን ታጠብ ብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የሳሙና ፋብሪካ ተከሉልህ... አንተ | 😇 xxxtentaction 😈😈🥰

እሳቸው ከመቶ አመት በፊት ገላህን ታጠብ ብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የሳሙና ፋብሪካ ተከሉልህ... አንተ አሁንም እሁድን ጠብቀህ ሻወር እየወሰድክ እሳቸውን ትሳደባለህ። በባዶ እግርህ አትንጦልጦል ብለው መኪና ከተባለ እጅግ ዘመናዊ ነገር ጋር አገናኙህ... አንተ ሰባት ዙር የሸገር ባስ ሰልፍ ተሰልፈህ Down Down Menelik ትላለህ። ተማር እወቅ ሰልጥን ብለው ትምህርት ቤት ገነቡልህ ከዘመናዊ ትምህርት ጋ አስተዋወቁህ... ከአራተኛ ክፍል አቋርጠህ ንጉሱ ላይ አፍህን ትከፍታለህ። ጥቁር በገንዘብ በማሸጥበት ዘመን "ደሀ የፈለገበት ይኑር" የሚል አዋጅ አውጀው ተዘዋውሮ የመኖር ነፃነትን አወጁልህ... አንተ ከሌላ ቦታ የመጣ ወንድምህን መጤ ብለህ በቆንጨራ ታሳድዳለህ.።
...
ብታውቅስ ምንሊክ እንደ ሀብል አንገትህ ላይ የምታስረው ጌጥህ ነው። አልሰልጥን ብለህ እንጂ አሰልጣኝህ ነው። አልማር ብለህ እንጂ አስተማሪህ ነው። እናም ከነ ድድብናህ ይመችህ። እንኳን አደረሰን