Get Mystery Box with random crypto!

ማን ያውቃል ? አንድ እድሜው የገፋ ገበሬ፡ እርሻውን የሚያርስበት አንድ ያረጀ ፈረ | 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

ማን ያውቃል ?

አንድ እድሜው የገፋ ገበሬ፡ እርሻውን የሚያርስበት አንድ ያረጀ ፈረስ ነበረው አንድ

ቀን ፈረሱ ከታሰረበት አምልጦ ወደ ጫካ ሸሸ። የገበሬው ጎረቤቶች በገጠመው መጥፎ እድል አዝነው ሲያጽናኑት

“መጥፎ አጋጣሚ ይሁን ጥሩ ማን ያውቃል?” ብሎ መለሰላቸው።

ከሳምንት በኋላም የጠፋው ፈረስ ብዙ የዱር ፈረሶችን አስከትሎ ከጫካው ተመለሰ። ይሄን ግዜ ደግሞ ጎረቤቶቹ በገጠመው ጥሩ እድል ደስታቸውን ገለጹለት።

“ጥሩ አጋጣሚ ይሁን መጥፎ ማን ያውቃል?” ነበር የገበሬው መልስ።

ከዚያ ደግሞ የገበሬው ልጅ፡ ከዱር ፈረሶቹ አንዱን ለማላመድ ሲሞክር፡ ከፈረሱ ጀርባ ወድቆ እግሩ ተሰበረ። የደረሰውን ክፉ አጋጣሚ ሁሉም ሲያማርር ገበሬው ግን

የተለመደ አስተያየቱን ደገመ፦

“መጥፎ አጋጣሚ ይሁን ጥሩ ማን ያውቃል?”
ከጥቂት ሳምንታት በኋላም የጦር ሰራዊቱ ወደ መንደሩ ዘልቆ፡ ጥሩ አቋም ያለውን ወጣት በሙሉ መለመሉ። የገበሬውን ልጅ ግን እግሩ በመሰበሩ ጥለውት ሄዱ።

ታዲያ ይሄ አጋጣሚ ጥሩ ነው ወይንስ መጥፎ? ማን ያውቃል?

https://t.me/kingnan