Get Mystery Box with random crypto!

ግድ የለሽ አትሁን ጎርፍ ሲወስድህ እያሳሳቀ ነው፤ ስንፍና በአንድ ቀን ከሰው በታች አያደርግህም | 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

ግድ የለሽ አትሁን

ጎርፍ ሲወስድህ እያሳሳቀ ነው፤ ስንፍና በአንድ ቀን ከሰው በታች አያደርግህም፤ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ የስንፍና ውሳኔዎች ግን ተጠራቅመው ነገ ዋጋ ያስከፍሉሀል።

ከዛ ገቢህን ስታየው ያንስብሀል ይሄ አይገባኝም ትላለህ፣ ስራህን ስታየው ውጤት አልባ ልፋት ነው፣ በምድር ለመደሰት አልታደልኩም ማለት ነው እስክትል ድረስ ህይወት አድካሚ ትሆናለች።

ህይወትህን እንዲህ አርጎ የሚያበላሸው ለነገ የምታሳድረው ስራ፣ ምንም ችግር የለውም ብለህ የተውከው የቀን ግዴታህና የማይረቡ ትንንሽ ውሳኔዎችህ ናቸው። ግድየለሽ አትሁን ትንሹ ጥረትህ ነው ትልቁን ውጤት የሚያመጣው!

መልካም ምሽት
https://t.me/kingnan