Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት_ስንቅ 'በመከራ ውስጥ ስታልፍ ወሳኙ ነገር ክብደቱ ቅለቱ ሳይሆን የምትሰጠው ምላሽ ነው!' | 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

የሕይወት_ስንቅ
"በመከራ ውስጥ ስታልፍ ወሳኙ ነገር ክብደቱ ቅለቱ ሳይሆን የምትሰጠው ምላሽ ነው!"
[አባት ለሴት ልጁ ካስተማራት]


#ልጅ ሕይወት ታክቷቷል። የኑሮ ውጣ ውረድ አድክሟቷል። ነባሩ ችግር ሲቀረፍ አዲሱ ይተካል። ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ሲሆኑባት ሕይወት እንደሰለቻትና እንዳማረራት ለአባቷ ነገረችው።

#አባቷ ሼፍ (ምግብ አብሳይ) ነበርና ወደ ማእድ ቤት ይዟት ገባ። ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ ማንደጃው ላይ ጣዳቸው። ከዚያም የመጀመሪያው ድስት ላይ #ካሮት፥ ሁለተኛው ድስት ላይ #እንቁላል፥ ሶስተኛው ድስት ላይ #የቡና_ፍሬ ጨመረበትና እሳቱ ላይ በደንብ አንተከተካቸው። [ይህ ሁሉ ሲሆን ልጅቷ ተመስጣ በዝምታ ትመለከተው ነበር።]

በመጨረሻም እሳቱን አጥፍቶ ካሮቱን እና
እንቁላሉን በማውጣት ዝርግ ሰሃን ላይ
አስቀመጠ። ቡናውን ደግሞ በስኒ ቀድቶ
አስቀመጠ። አባት ለልጁ ካሮቱን እንድትነካው አስጠጋላት። ልጅ ነካካችው እንደ ለሰለሰአስተዋለች።

አባት እንቁላሉን ሰብራ እንድትመለከተው
ነገራት። ሰብራ ተመለከተችው ከቅርፊቱ በታች ያለው ውስጠኛው ክፍል ጠንክሯል።

ቡናውን ፉት እንድትል አዘዛት ቀመሰችው ጣእሙ ድንቅ ነበርና ፈገግ አለች።

ልጅቷም አባቷ ለምን እንዲህ እንዳደረገ ግን አልገባትምና " አባቴ ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ይሄ ከእኔ ጋር ምን አገናኘው? ትርጉሙን ንገረኝ አለችው?"

አባቷም እንዲህ አላት፦ " ልጄ ሶስቱም ነገሮች ተመሳሳይ ነገር ገጥሟቸዋል። ሁሉም በሚፈላው ውሃ ተቀቅለዋል። ነገር ግን የእያንዳንዳቸው ምላሽ የተለያየ ነበር።

ካሮቱ የቀድሞ ጥንካሬውን አጥቶ ደካማ ሆኗል። እንቁላሉ በላይኛው ቅርፊቱ የሚንተከተከውን ውሃ የተቋቋመ ቢመስልም ውስጠኛው ፈሳሹ ግን
በመኮማተር ጠጥሮ ነበር። የቡና ፍሬዎቹ ይለያሉ ምንም እንኳን ቢቀቀሉ ውሃውን መቀየር ችለዋል።

አንቺ የቱ ነሽ? መከራና ችግር ፈተና በርሽን ባንኳኳ ጊዜ እንዴት ነው ምላሽ የምትሰጫቸው? እንደ ካሮቱ እንደ
እንቁላሉ ወይስ እንደ ቡናው? በደንብ አስቢ።

ጠንካራ የምትመስይ መስለሽ ነገር ግን መከራ በመጣ ጊዜ እንደ ካሮቱ
ልፍስፍስ ሆነሽ ትገኛለሽ?

እንደ እንቁላሉ በቀላሉ ሃሞትሽ ፍስስ የሚል የሚኮራመት ልብ ያለሽና ውጫዊ ገፅታሽ እንዳለ ሆኖ ውስጥሽ ግን በምሬት የተሞላሽ ነሽ? ወይስ

እንደ ቡናው ፍሬ የቱንም ያህል ችግር፤ ፈተና፤ ስቃይ ቢገጥምሽ አስከፊ መከራ ቢደርስብሽ ጣእምና ቃናሽን በመለገስ አካባቢሽን የምትቀይሪ ነሽ? ራስሽን ተመልከቺው አንቺ የቱ ነሽ?

ልጄ ዋናው ነገር ምን መሰለሽ? ፈተናና
መከራ ሲመጣ ወሳኙ ነገር ክብደቱ ቅለቱ
ሳይሆን የምንሰጠው ምላሽና አቀባበላችን ነው የሚወስነው። " ሲል ስለ ሕይወት አስተማራት።

እስኪ ልጠይቃችሁ እናንተስ ፈተና፤ ችግር፤ ስቃይ፤ መከራ ሲገጥማችሁ እንዴት ነው ምላሽ የምትሰጡት እንደ እንቁላሉ ካሮቱ ወይስ እንደ ቡናው? የትኛውን ናችሁ?

https://t.me/kingnan