Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት! ....የቀጠለ (5) ከዚኽን በፊትም በተለ | ንቂ ኢትዮጵያ

ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

....የቀጠለ

(5) ከዚኽን በፊትም በተለመደው የፖለቲካ ሴራ አካሔድ መሠረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበር አውርደው በሌላ ተረኛ ለመተካት ባለሥልጣናቱ ፊት ለፊት መምጣቱን አልፈለጉትም፡፡ እናም፥ መጀመሪያ ቅዱስነታቸውን እነርሱ ‹‹ጁንታ›› ከሚሉት አካል ጋር ፈርጀው ለማሸማቀቅ፣ በምእመኑ ዘንድ ለማስጠላትና ‹‹በፈቃዳቸው ለቀቁ›› ለማስባል ሞከሩ፡፡ ‹‹እኔም ኦርቶዶክሳዊ
ነኝ›› የሚሉ፣ በተግባር ግን ያልኾኑ ‹‹መምህራን›› እና አክቲቪስቶችን ከጀርባ ‹‹አይዟችሁ!›› እያሉ በጸያፍ አገላለጾች አስሰደቧቸው፤ ከልክ በላይም አፍ አስከፈቱባቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን
ዋና ጸሐፊ ‹‹አይወክሉንም!›› የሚል መግለጫ አስሰጡ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ግን በሚገርም ኹኔታ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ‹‹ከአባታችን ጎን ነን!›› ብሎ አሳፈራቸው፡፡ ይኽንን የሕዝቡን ሥነ ልቡና ያስተዋሉት ፖለቲከኞቹ ከቅዱስነታቸው ጋር የ ግል ቅራኔ ያላቸውንና የሥልጣን ጥም ያሰከራቸውን ‹‹ጳጳሳት›› በኅቡዕ አደራጅተው መንቀሳቀስ ይዘዋል፡፡ ‹‹ደኅንነቶች ነን›› በሚሉ ሰዎችና ለተረኛው መንግሥት እንቀርባለን በሚሉ ‹‹አባቶች›› አማካይነት ‹‹መንግሥት የሚፈልገው ይኽንን ነው›› ብለው እያስወሩ በአባቶችን ውሳኔ ላይ ከወዲሁ ጫና ለማሳደር እየተሞከረ፣ ቤት ለቤትም ቅስቀሳዎች እየተደረጉ መኾኑ እየተሰማ
ነው፡፡ ገና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳይሰበሰብም፡- ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ በሌሉበት ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሔድ፣ እንደራሴ እንደሚሾም›› ማስወራት ይዘዋል፡፡ የእኛን አባቶች እየተዋጓቸው ያሉት በእኛው አባቶች ነው የሚያስብለውም ይኸው ነው!

(6) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በማርቀቅና በማጽደቅ ሒደት ውስጥም የግለሰቦች ፍላጎትና የውጭ አካላት እጅ እየገባ እንደኾነ ተሰምቷል፡፡ ገና ሕጉ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ሳይጸድቅ ‹‹የማስፈጸሚያ ሰነድ›› የሚል ረቂቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ባሉት የወቅቱ ፈላጭ
ቆራጮች አማካይነት ሌላ አጀንዳ ማስቀየርያ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡ ስሙን ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን›› እያሰኙት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለግለሰቦች ፍላጎት አሳልፎ የሚሰጠውን አካሔድ ግን ‹‹ሕጋዊ›› ለማስመሰል የሚሔዱበት ርቀት ያስተዛዝባል! ሌላው ቀርቶ ‹‹እኛ
መነኮሳት ነን፤ ንብረታችን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን እንጂ የእኛ መኾን የለበትም›› የሚል ሐሳብ የሰጡ ሊቃነ ጳጳሳትን እንኳን ምን ያኽል ሲያገልሏቸው እንደነበር የምናስታውሰው ነው!

(7) የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነትና መዋቅራዊ ጥንካሬ ለጎሣ ፖለቲካቸው የመከፋፈል ሴራ አልመች ሲል የ16ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን እሾኽ (‹‹ቅብዓት›› የሚባል ኑፋቄ)
በ21ኛው ክፍለ ዘመን መልሰው ለመትከል ምሥራቅ ጎጃምን የሚያስጨንቋትም አሉ፡፡
በየትኛውም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሥርዓት ‹‹ጳጳሳት›› እንደተሾሙ ተነገረ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብና አጀንዳውንም ለማስቀየርም ሲሉ ‹‹የጳጳሳቱ በዓለ ሢመት ተዘጋጅቷል›› ብለው የጥሪ ካርድ በተኑ፡፡ ይኽ ኹሉ ሲኾንና ከመደበኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ተደጋጋሚ አቤቱታ ለመንግሥት መዋቅሮች ሲቀርብ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል፤ በአጥፊው ፋንታም ሰላማውያኑ ታስረዋል፡፡ ‹‹ተለያይቶ
የነበረውን ሲኖዶስ አንድ አደረግሁ›› ብለው የሚመጻደቁት አካላት ‹‹ሌላ ሲኖዶስ›› ለመፍጠር ለምን እንደሚሯሯጡ ግን ግልጽ አይደለም!
ኦርቶዶክስን በራሳቸው በኦርቶዶክሳውያን አማካይነት የማዳከም ስልት፤ አዲሱ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሴራ!

ከ ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፣ ምዕ.4፥ ገጽ.89-92 ላይ ባለው ሐሳብ መነሻነት የተጠናቀረ