Get Mystery Box with random crypto!

ውሎ አዳር በጎንደር (ታመነ መንግስቴ ነኝ) ስሆነው ፣ሳደርገው የዋልኩትን በሰንበት ላውጋችሁ! | ንቂ ኢትዮጵያ

ውሎ አዳር በጎንደር

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

ስሆነው ፣ሳደርገው የዋልኩትን በሰንበት ላውጋችሁ!

ይችን እሁድ የምትሰኝ ዕለት ፈጣሪ እኛን አበጅቶ እርፍ ብሎባታል ሲባል እሰማለሁ፣አንብቤማለሁ።

"ብታምኑም ባታምኑም ጦር ግንባር ሳለሁ ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ለኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ደውየ የግድቡን ሁኔታ እጠይቅ ነበር" እንዳሉት የአገሬ መራሔ መንግስት(ሀሳብዎ ላይ ተሳስቸ ያላሉት ነገር ብየ ተሆነ እርስዎ ተሳስተው 'የኤርትራ ጦር አልገባም' እንዳሉት ይቁጠሩት) እኔም 'ብታምኑም ባታምኑም እሁድ የእረፍት ዕለት ናት' ብያችሗለሁ።

ግን ግን ጠቅላያችን "ነገርዮሹ ስራዎት መስሎኝ? ለምን ማሳመን አስፈለገዎት_እያ!?"

ደሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን የሚሉት አለማመን ነው? አሁን እኒህ የመኪናችን ዘዋሪ እስላሙ፣ጠዋት ቁርጥ ስንበላ'ቁርስ በልቻለሁ' ያሉን ኦርቶዶክሱ ጓዴ መኪና ውስጥ መተኛትን ተልባቸው መያዛቸውን ለማረጋገጥ 'ማርያምን?' ሲላቸው 'ማርያምን' ብለው የለም? ቢራስ አብረን አልጠጣንም? ይህችን እንቆቅልሽ አገር ምን ማድረግ ይሻላል? ማሳደግ

ውሎ አዳር በጎንደር፦

"ምን ተሰራ ፤ምን ተወራ
ጎንደር በጀግኖች ጎራ?
ይበሰራ፣
እውቀት ሐቅ ይነገራ።"

በሚል ዘፈን ተጀመረ።የመፃፍ ጸጋየን ተጠቅሜ "የጎንደር ወዳጆቸ ጋሽ ንዋይ"ጎንደር የወርቁ ልጅ ዘውዴ ናት እናቴ!" ያለላትን በሙሉ ስሟ ዘውዴ ወርቁ የምትሰኘን የጎንደር እናት ፈልጋችሁ አገናኙኝ " ብየ ለመንኩ።ልመናየን የሰማው እግዜር(እግዜር ግን ያነባል?) ቃልኪዳን(ቃልየ ብየ ስሟን አላቀልም) የዘውዴን ምትክ ፍቅርን አገናኙኝ።ፍቅር እኮ የባለከዘራው እህት ናት።እዚያ ቤት ያጎረሰችኝን ልጅ እግዜሩ መና ያውርድላት።እግዜሩ ግን ሳልሞትበት ለአፋር ሕዝብ የሚያጠግብ ውሃም ይስጠው።

ቀኑን ሙሉ ስንፈልገው የዋልነው ሰውየ ደመቀ ዘውዱ አይደለም? እኔስ ቤቱን፣ሚስቱን፣ልብሱን፣ጉርሱን አይቸ"እንደሰው ነው የምትኖር ጋሸ!?" ብየ ብደነቅበት "እህ እንደምን ልኑር?" አለኝ።

እኔማ እንደ 'ከንቲባ' አዳነች አበቤ ብየ ነበር።እናንተ 'እዳነች አበበች'የምትሉ ነገር ሰንጣቂዎች ግን ለአማራ ሕዝብ ምን አድርጋችሁለታል?

"አማራው ያጣው መሪ ነው።መሪዎች ለራሳቸው ክብር እንጅ ለሕዝቡ አይጨነቁም።"ብላችሁስ 'ማን አለህ'? ልትሉኝ አይደል?

'ደመቀ ዘውዱ' ልበላችሁና ዳግም አስከብቡት! እናንየ 'ጎንደር ባለ ማተብ ነው፤በደመቀ ዘውዴ እና ወልቃይት ጠገዴ አይደራደርም።'

የልቅ እንየ ታከለ የባህል አዳራሽ ብቅ ብለን እንመለስ። እዚያ 'ዶፔል ቢራ 22 ብር' ተብሎ ዋጋው በር ላይ የተፃፈለት ምን ያህል አስቀያሚ መጠጥ ቢሆን ነው? ጣፋጭ መጠጥና ልባም ጎንደሬ እማ 'ሽሽግ' ተደርገው እንደ መይሳው ካሳ ላለው የአገር ዋልታ ይሰጣሉ።የራስ አሊ እናት ተዋበችን ለዳግማዊ ቴዎድሮስ የዳሩለት እኮ ዋጋዋን ለጥፈው አይደለም!

'አንች በቀሚስ የምትዋቢው ጎንደሬ ወዳጀ እነበብሻለሁ!?"

"እኔን ጎንደር ጎንደር እኔን ጎንደር ያርገኝ
የበሉት ሲስማማ የፈለጉት ሲገኝ"

የባለከዘራው እህት ቤት የበላሁት እዚህ የማይፃፍ ነገር ተስማምቶኛል።እንደምሳ በልቸው እነሆ ራትም ሆኖኛል።ኤርምያስ አመልጋ ለምን በ24 ሰዓት አንዴ ብቻ እንደሚበላ ተገለጠልኝ ልበል እንዴ? ይልቅስ 'ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ማዕከላዊ እስር ቤት ነበርኩ" ያለኝን መኩሪያ የሆነ ፋኖ_ሻለቃ ጠዋት ቃለ መጠይቅ አድርጌ አለሁ።

አዝማሪ አማረን...!

እንየ ታከለ ቤቷ ሞልቶባታል።ባልደረባየ"እናንተ ፈስሳችሁ ነው?" ያላቸው ጎንደሬዎች(ተሌላም አገር ሊመጡ ይችላሉ።አርብ ዕለት አዘዞ ጥይቱ እንደፈነዳ ዘብ(Police )ጣቢያ ተመቶ ሁለት ሰውም ሞቶ ገብተን ወላ ሐድያ ወላ ወላይታ ብቻ ሴቶች ለስደት ሊያመልጡ ሲሉ ተይዘው አላየንም እንዴ?) በሩን አልፈው መንገዱን እየዘጉት ነው።

ተስፋ ቆርጠን('ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም'ሲባል እሰማለሁ።እስላምስ? እሱም አይቆርጥም።አብሮን የነበረው ሰውየ እስላም መሆኑን ተላይኛው አንቀጽ ጥፌ የለም እንዴ?) ስንጓዝ "ባላገሩ " የሚሉት የአዝማሪ ቤት አገኘን።

"እኔን ጎንደር ያርገኝ"

እዚያ ቤት ገብተን የገበየነውንስ ታልሞትኩ ተድሉ በሗላ አወጋችሗለሁ።ተሞትኩም አትደነቁ ሌላ ታመነ ወይም ሌላ እገሌ ያወጋችሗል።

"ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም።" ጎንደርም በላሊበላ ዘመን ዝም ብላ ጋራ እና ሸንተረር ነበረች።ሗላ "እሽሩሩ ጎንደር"ተባለች።የፋሲል ግቢን አሃለች።አሁንም ደርግና ወያኔን ተቋቁማ እየቆዘመች፣እያስቆዘመችኝ አለች።

t.me/Gazetaw