Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት አጋሬን እንዴት ልምረጥ “ፍቅር ይዞኛል” “አፍቅሬአለሁ” ማለት በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተ | ✞ ኪዳነ ምህረት እናታችን ✞

የሕይወት አጋሬን እንዴት ልምረጥ

“ፍቅር ይዞኛል” “አፍቅሬአለሁ” ማለት በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ወጣትነትወንዶች ሴቶችን ሴቶችም ወንዶችን ለፍቅር የሚመርጡበት እድሜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመንበተቃራኒ ጾታ መሳብ፤ የራስን ሰው ለማግኘት ጊዜ ወስዶ ማሰብና መጨነቅ የተለመደ ክስተትነው፡፡ መፈላለግ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሁሉም ለቁም ነገር ነው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ በዚህየተነሣ ወጣቶች ተቃራኒ ጾታን ለጓደኝነት የሚመርጡባቸውን ምክንያቶች በሚገባ ማወቅ አስፈላጊ ያቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን ምክንያቶች በዚህ ትምህርት ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. ወጣቶች የተቃራኒ ጾታ ጓደኛ የሚይዙባቸው ምክንያቶች
ሀ. ጓደኛ የለውም (የላትም) እንዳይባሉ፤
ለ. ሌሎች ሲይዙ በማየት፤
ሐ. ለሩካቤ ሥጋ ፍላጎት (ለዝሙት) (2 ሳሙ 13፡11)፤
መ. በፍቅር ስለወደቁ (ዘፍ. 34፡3)፤
ሠ. የትዳር ጓደኛ ፈልገው (ዘፍ. 29፡18)፤
ረ. ለቁሳዊ ጥቅም ብለው (መሳ. 16፡5)
ሰ. በፉክክር ስሜት፣ ሌሎችም ለማናደድ ሲፈልጉ ወ.ዘ.ተ፡፡

2. የሕይወት አጋርን የምንመርጥባቸው ደረጃዎች፡-ወጣቶች የፍቅር ጓደኛ መፈለጋችሁ ኃጢአት ሳይሆን ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ ስሜት ነው፡፡ነገር ግን ይህን የተቀደሰ ፍላጎት ያለ ጊዜው፣ በተሳሳተ ምርጫ እና ጤናማ ባልሆነ ፍላጎት እንዳናበላሸው ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መመዘኛዎችና ደረጃዎችን ማጤን ትክክለኛ ውሳኔ እንድንወስን ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ያለጊዜው ባደረግነው ያልተገባ ግንኙት ወይምበተሳሳተ ምርጫችን እንዳንጸጸት ያደርገናል፡፡

2.1. አካላዊ ብቃት፦
ወንዶች ለአቅመ አዳም ሴቶች ለአቅመ ሔዋን መድረሳችንን፤ ሰውነታችን ሌላ ሰውን ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡

2.2. መንፈሳዊ ብስለት፡-
በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንካራ መሆናችንን እንዲሁም ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ መንፈሳዊብስለት እንዳለን ለማረጋገጥ ራሳችንን ማየት ተገቢ ነው፡፡ በሕይወታችን ወይም በኑሮአችን ሁሉእግዚአብሔርን እንደምናስቀድም፣ የጸሎት ሕይወታችን ምን እንደሚመስል፣ መጽሐፍ ቅዱስንየማንበብና ለቃሉ ያለንን ፍቅር፣ የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ጥንካሬ … ወ.ዘ.ተ ያጠቃልላል፡፡

2.3. የኢኮኖሚ ብቃት፦
ፍቅር ሓላፊነት እና ተጠያቂነት ያለበት ግንኙነት ነው፡፡ ገንዘብ ለዚህ ዓለም ኑሮ አስፈላጊ ነገርነው፡፡ ስለዚህ ከራሳችን አልፈን ሌላ ሰው ማኖር እንዲሁም መንከባከብ የሚያስችል አቅም አለኝ ወይብለን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ለመተዳደሪያ የሚሆን በቂ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ አለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ መመለስ ይገባናል፡፡

2.4. የሥነ ልቡና ዝግጅት ፦
አንድን ሰው ለማፍቀር ከመነሣታችን በፊት ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት ማድረግ አለብን፡፡ ፍላጎታችንን መመርመር፣ ሌላ ሰውን ለመቀበል የመንፈስ ዝግጅት ማድረግ፣ በስሜት ሳይሆንበእርጋታና በሰከነ መንፈስ ምርጫችንን ማጤንን አስፈላጊ ነው፡፡

ወጣቶች የሕይወት አጋራችሁን ስትመርጡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላታችሁን አረጋግጡ፡፡ ፍቅር የከበረ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ተገንዝባችሁ በስሜታዊነትየፍቅር ጓደኛ ከመምረጥና በኋላ ከመጸጸት ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ከክፉ የጎልማሳነት (የወጣትነት) ምኞት በመራቅና በመሸሽ እያንዳንዱን ጉዞአችሁን በእግዚአብሔር ቃል እየመረመራችሁ እናፈቃዱን እየጠየቃችሁ በመንፈስ የምትመሩ ሁኑ፡፡

https://t.me/kidanemihiret2116