Get Mystery Box with random crypto!

ዙልሂጃ 11 የዒድ ማግስት'የውሙል ቀር' ማለትም ሁጃጆች ሚና ላይ ተረጋግተው የሚቀመጡበት ዕለት ሲ | ኹበይብ መስጂድ\ مسجد خبيب

ዙልሂጃ 11 የዒድ ማግስት"የውሙል ቀር" ማለትም ሁጃጆች ሚና ላይ ተረጋግተው የሚቀመጡበት ዕለት ሲሆን ይህንን ቀን አስመልክተው የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ዘንድ ከሁሉም ከቀናቶች በላጩ ቀን የውሙ ነሕር(የዒደል አድሓ ቀን) ነው።በመቀጠልም የውሙል ቀር።" አቡዳዉድ ዘግበውታል አልባኒ ሰሒህ ብለውታል።
አቡ ሙሳ አልዐሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የዒድ ቀን ኹጥባ ሲያደርጉ እንዲህ ብለዋል፦
"ከዐረፋ ቀን በመቀጠል ሦስቱ ቀን የዚክር ቀናት በነዚህ ቀናት የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት አለው።ስለዚህም ክጃሎታችሁን ወደ አላህ ከፍ አድርጉ ።" 【ተፍሱሩ አጠበሪይ (4/203—206)】

ዒክሪማ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ብለዋል ፦ «ሰሓቦች በነዚህ አያም ተሽሪቅ ቀናት ይህን ዱዓ ያበዙ ነበር። "ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺራ ሐሰነተን ወቂና አዛበ አንናር።»
{ኢብኑ ረጀብ (ለጣኢፍ አልመዓሪፍ)}

http://t.me/khubeybmesjid