••●○ ሌላ እንዴት ያፍቅርሽ ●○•• ፈጣሪ ውብ አርጎ ከነ ደም ግባትሽ፤ ከዝምታሽ እኩል እንዲናፈቅ ድምጽሽ፤ በፍቅር ህገ ደምብ ስንቱን ሀገር ገዛሽ። ባንቺ ህግና ደምብ ባንቺ ንግስና ስር፣ ከጥንት ዠምሬ እተዳደር ነበር። ያፈቀረ ይሙት ፣ ፍቅሩን ሀብል ሰርቶ አንጠልጥሎ ይገትት፣ የሚል ህግ እንዳለሽ ለምን ሳይካተት፣ ከደምቦችሽ መህል ደምብ ቁጥር ሰጥተሽ፣ አንቀፅ አብጅተሽ፣ አስገቢው በናትሽ፣ እኔ ላንቺ ሞቼ ሌላ እንዴት የፍቅርሽ። አንዋር የሱፍ ╔═══❖• •❖═══╗ @kezim_kezam ╚═══❖• •❖═══╝ 4 any comment @kezim_kezambot ❥❥________⚘_______❥❥ 1.2K views༄᭄✮ًٍٜ͜͡𝐃𝐚𝐠𝐢 𝐃✮ًٍٜ͜͡𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ ᭄࿐, 12:23