Get Mystery Box with random crypto!

​••○● ስደቢኝ_ግድየለም ●○•• ስደቢኝ ግድየለም አልቀየምሽም ደደብ የማትረባ አህያ ነህ ቀሽም | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​••○● ስደቢኝ_ግድየለም ●○••

ስደቢኝ ግድየለም አልቀየምሽም
ደደብ የማትረባ አህያ ነህ ቀሽም
ሲጠሉህ የማታውቅ እልም ያልክ ፋራ
ልክስክስም በይኝ አስቀያሚ ጭፍራ
ከፈለግሽ ደግሞ ደሀ ለቃቃሚ
ብትይኝ ግድየለም እባክሽን ስሚ
.
ከስድቦችሽ መሀል መልካሙን እያየሁ
ፋራ በመሆኔ እጅጉን እኮራለው
አህያ ላልሺኝ ደግሞ አንቺን ተሸክሜ
እስከዛሬ አለሁ ይሄውልሽ ህመሜ
.
ደሀ ነህ ብለሻል ደሀ ነኝ አውቃለው
ሀብታም ስላልሆንኩኝ አመሰግናለው
ምናልባት ግን ሆዴ.....
ገንዘብ ኖሮኝ እኔ በሀብቴ ብኮራ
ስድብሽን ሰምቼ እለይሽ ነ'በራ
ሁሉን ያጣ ሆኜ ብትይኝ ውዳቂ
እንደማልጠላሽ ግን አሁንም እወቂ፡፡


•○● ከዚህም ከዚያም ●○•
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም