Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​ ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት የውበት ዳርቻ የአድማሷን መባቻ | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​​​​​​​​​​

ብልጡ ፍቅርሽ ሲያጃጅለኝ የጫርኩት


የውበት ዳርቻ
የአድማሷን መባቻ።
አንቺን የእኔን ጠሀይ
የተድላዬን ሰማይ።
ልስልሽ ፈለጌ
ምስልሽን አጣሁት
ከምስሌ አድርጌ።

ከስብዕናሽ ጠለል ከሀሳብሽ ከፍታ
አየሁኝ በሳቅሽ ጨረቃ ተከፍታ።
ጨረቃ ጨረቃ
ጨረቃ ጨረቃ
ያቺ ድንቡል ቦቃ
አንቺ ስትፈዢ ይሆን ምትነቃ?

አንቺ እንደሁ አትፈዢ
ከቶ አደበዝዢ
በመውደድሽ ሸጠሽ ታደርጊያለሽ ገዢ።

ያውም በሠላሳ
ያውም በሠላሳ

ክደሸ ስታበቂኝ ምንም እማልመስልሽ
በገደልሽኝ ቁጥር ሳትሞች ምሞትልሽ
በገፋሽኝ ቁጥር ሳትወድቂ ማነሳሽ
በሸጥሽኝ መጠን ልክ ለመክሰር ምገዛሽ
ይሁዳ ነሽ አንቺ እኔ ደግሞ ጌታሽ።

መልአኩ ስብሐት ባይህ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ከዚህም ከዚያም TUBE

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ