Get Mystery Box with random crypto!

ህቡዕ ገጽ ህቡዕ ገጽ ህቡዕ ገጽ | ኬልቅያስ

ህቡዕ ገጽ
ህቡዕ ገጽ
ህቡዕ ገጽ

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
ክፍል አንድ

ፀሐይ በደመና ተጋርዳ ሰማዩ ጥላ አጥሏል። አየሩ ነፋሻማ ምቹ ስለነበር ህዝቡ ከፊታቸው በእንባ እየታጠበ የሚሰብከውን ሰባኬ ወንጌል ጸጥ ረጭ ብሎ ያደምጠዋል። ሕፃናት ሳይቀሩ በመምህሩና ከሕዝብ መካከል በሲቃ እየታፈኑ ከሚያነቡት ከብዙዎቹ ማንባት ምን መጣ በሚል ተደናግጠው ተቀምጠው ሰባኪውን ዓይን ዓይኑን ያያሉ።

""" ኢካቦድ""" ክብር ከእስራኤል ለቀቀ። ቀደምት የስልጣኔ ምድር የጥበብ አሻራ የቅዱሳን ምድር የድንግል አስራት ሀገረ እግዚአብሔር ኢት.....ሳግ አነቀው.....ዮጵያ""ፊደላቱን አምጦ ወለዳቸው።
""""ዛሬ ለምንድነው የጦርነት ምድር የደም መሬት የሆነችው?
እንግዳን ተቀባይ የነበረች ምን ነክቷት ነው ልጆቿን ረሀብ የሚቀጣቸው?
ለምንድነው ወንድም በወንድሙ ጨክኖ ሾተል የሚስለው? ቃታ የሚስበው?
ለምንድነው ክርስቲያኖች የመከራ ሽልማት እጩዎች የሆኑት?""""

ጉባኤው ሆድ ባሰው ህዝቡ የገረፉት ሕፃን ይመስል እየተንሰቀሰቀ በለቅሶ እንባ ፊቱን ያጥባል። ሰባኪው በዓይኑ እየቃኘ በእንባ አይኖቹ ፍም መስለው ቀጠለ። አሻግሮ ሲመለከት እርምጃቸው የተለየ ሁለት ሰዎች ከውጭ ሲገቡ አየ። ሰዎቹ ከአንድ ትልቅ አጸድ ስር ሳይሳለሙ ተደግፈው ቆሙ። ስብከቱ ቀጠለ።
""" ኑ እናልቅስ ኑ እንመለስ ኑ ወደቤታችን እንግባ ኑ እናንባ አንተ ሰበርከን ኑ አንተ ጠግነን እንበል። ኑ በንሰሐ ዳግም እርቅ እንፍጠር። ኑ ሀገር እናንሳ ኑ ሀገር እንሁን ኑ ፍቅርን እናንግሥ ኑ ጥላቻን እንቅበር።""

አንዳንድ አረጋውያን በነጠላቸው እንባቸውን ጠረገው ቀና ሲሉ ሲያይ ሰባኪው የእንባው ጅረት ይጨምራል። እንዲያም እያነባ ቀጥሏል። ወደ መግቢያው የውጭ በር ሲያይ አንድ ትጥቅ የታጠቀ የፖሊስ ልብስ የለበሰ ሰው ስልክ እያወራ ገብቶ አጸዱን ተደግፈው ከቆሙ ሁለት ሰዎች ጋረ ሰላምታ ተለዋውጦ ቆመ።
"" ሰባኪው ዛሬ አስቦ ወደመድረኩ የወጣው ሌላ ርዕስ ነበር። አሁን የሚሰብከው ርዕሱም ያላሰበው ስለነበር የሚናገራቸው ቃላቶች ሁሉ ከሌላ እንዲሰማው ሆነው እየተሰሙት ልቡ ተነክቶ እንባው ገደብ አቷል። "" የእግዚአብሔር ቤተሰዎች"" አለ ሰባኪው። "" በእኛ የሆነው እርግጥ ከባድ ነው።""

ሰቆ ኤር 5:16-17 እንዲህ ይላል"" አክሊል ከራሳችን ወድቆአል ኃጢአት ሰርተናልና ወዮልን! ስለዚህ ልባችን ታምሞአል ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዞአል።""" ከመጽሐፍ ቃሉ ሲነበብ ለካ ጉዳችን ከዚህ ተጽፏል በሚል ለቅሶው ከሕዝቡ ቀጠለ። ሰባኪው በቃለ ተማጽኖ ትምህርቱን አጠናቆ ተቀመጠ።

ቀጣይ "ማረን አባታችን" የሚል የንሰሀ ዝማሬ ጥኡም በሆነ ለዛ ባላት አንዲት ዝማሬ ቀርቦ ሌሎችም ዝማሬዎች ተዘምረው በጸሎት ጉባኤው ተጠናቀቀ።

ሰባኪው ከነበሩት አባቶች በእድሜ ከገፉት ተባርኮ ተሰናብቶ ሲሄድ አንድ ፀጉሩ የተንጨባረረ ወጣት "መምህር" ሲል ሰባኪው ቆመ። " ይቅርታ!! አንተ እያልኩ ባወራህ...."" ሲል "" ችግር የለውም" አለው። ወጣቱ ""ስሜ ከነዓን ይባላል"" ብሎ እጁን ሲዘረጋ ሰባኪው " ንፍታሌም" ብሎ ጨበጠው። " መምህር የማወራህ ምሥጢር እና ጥቂት ጥያቄ ነበረኝ" ሲል ተሰናብቶ የሚሄደውን ሕዝብ አቋርጣ አንዲት ቆንጆ ልጅ "" አሁን የሰበከውን መምህር ሊያስሩት ነው። ብዙ ፖሊሶች ደጅ ቆመዋል መኪናቸውም ደጅ ቆማለች አጸዱ ጋር የቆሙት ሶስት ሰዎች ሲዝቱ ሰምቻለው።"" እያለች ድምጿን አሰምታ እየተዋከበች ሰባኪው ጋር ደርሳ "" አምልጥ ከጀርባ ውጣ ይገድሉሀል"" ስትለው እየወጣ የነበረው ሰው ሁሉ ከጥቂቶች በቀር ወደ ኋላው ተመለሰ።
"" እኛን ሳይገድሉ አይዙት መቼም" አሉ መቋሚያ የያዙ አንድ አዛውንት። ሌላውም ሰው ሁሉም እርስበርስ እያጉረመረመ ሌላው ጥግ ይዞ ግማሹ ወደ ሰባኪው ሲያቀና ከአጸዱ ስር የነበሩ ሶስት ሰዎች ሰባኪው ወዳለበት መራመድ ጀመሩ። ከውጭ ያሉ በርካታ ፖሊሶችም ወደ መግቢያው በር ተጠጉ።
"" አይዞሽ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው ይጠብቀኛል።" ብሎ ይሸሻል ብላ የጠበቀችውን ቆንጆ ልጅ ትከሻዋን ቸብቸብ አደረገና ወደረሱ ወደሚመጡት ሶስት ሰዎች መራመድ ጀመረ። ከሶስቱ አንዱ ትጥቅ የታጠቀው "ሌሎቻችሁ ሂዱ ግቡ" ሲል አንድ የሰማይ ስባሪ የሚያህል የፈረጠመ ወጣት ሶስቱ ሰዎች ፊት ቆሞ "ከመምህራችን ፊት ሞታችን ይቅደም ኢኸው ግደሉኝ።" ሲል ሌሎችም ተከታትለው ፊታቸው ቆሙ።

ሰባኪው አጠገባቸው ደረሶ "ማንን ትፈልጋላችሁ?"" ሲል መቋሚያ የየያዙት ትልቅ አዛውን "እኔ ልሙት ልጄን ምን ባጠፋ?" አሉ እያለቀሱ። "ለጥያቄ ጣቢያ ፈልገን ነው እባክህን ሌሎችም ባልደረቦቻችን መኪና ይዘው እየጠበቁን ነው። መምህር ማነው ስምህ ?" አለ ሌላው ከሶስቱ። ከውጭ ሆነው ለሁለት ተከፍለው ሲከራከሩ ከነበሩት ገሚሶቹ ህግ አስከባሪዎች ወደ ቤተክርስያኑ ግቢ ገብተው ወደ ተሰባሰበው ሰው አቀኑ።
2014 - ሐምሌ- ሐሙስ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል