Get Mystery Box with random crypto!

ታቅፌው እንድውል ፍቀጂልኝ ታቅፌው እንድውል ፍቀጂልኝ ድንግል ሆይ ወዳንቺ መ | ኬልቅያስ

ታቅፌው እንድውል ፍቀጂልኝ
ታቅፌው እንድውል ፍቀጂልኝ

ድንግል ሆይ ወዳንቺ መጥቶ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደኔ ይምጣ።

ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት። ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል? ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምህረት ይምጣ።

በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምህረት በእኔ ላይ ይውረድ። የኃጢአት አሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ።

ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቅፈሽው ነበር። እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እርሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጅልኝ።

!! አሜን !!