Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እ | ቀለሜ_2015

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚችሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በክልሉ ለፈተና ከተመዘገቡ 451 ሺህ 21 ተማሪዎች
ውስጥ 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተናውን መውሰዳቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ተናግረዋል።

በዚህም የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ፤ ለሴቶች 47 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ አርብቶ አደሩ አካባቢዎች ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 47 በመቶ፤ ለሴቶች 44 በመቶ ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44 በመቶ፤ ለሴቶች 41 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በተከታዩ ሊንክ መመልከት ይችላሉ፦

https://oromia.ministry.et/#/home

#tikvahuniversity
https://t.me/keleme_2014