Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳን ገዳማት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kedusangdamat — ቅዱሳን ገዳማት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kedusangdamat — ቅዱሳን ገዳማት
የሰርጥ አድራሻ: @kedusangdamat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 398
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌ ግራም ቻናል
• በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሚገኙ ቅዱሳን ገዳማት እና አድባራትን ማስተዋወቅ,,, ☆
• የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ማስከፈት እና መልሶ ማቋቋም
• የአብነት (የቆሎ) ትምህርት ቤቶችን ምንጩ እንዳይደርቅ መደገፍ….. እና ሌሎችንም መንፈሳዊ አገልግሎቶች ያከናዉናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-19 20:43:37 "ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ"

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ ★ ለሁሉም የተዋሃዶ ልጅች እንዲዳረስ #ሼር #ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ይቀላቀሉን★

╭══ ❀:✧๑♡๑✧❀ ══╮
@kedusangdamat
╰══ೋ•✧๑♡๑✧ ══╯
238 viewsEskedar Zeleka, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:38:41 ለኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው

ለኔ ያደረገው ሚካኤል ብዙ ነው (2)
ከእግዚአብሔር ተልኮ ድንቅ አደረገልኝ
አፅናኝና እረዳት ሚካኤል ሆነልኝ

አዝ =========

ታናሽ ብላቴና ስምክን የማይረሳ
ደግፈኝ ሚካኤል ስወድቅ እንድነሳ
ስምህን በልቤ ፅላት እፅፋለሁ
በክንፎችህ ጥላ ዛሬም ድረስ እላለሁ

አዝ ==========

ውለታህ እንዳይጠፉ ሁሌም ከሀሳቤ
ሚካኤል ሳልልህ ፍቅርህን ከልቤ
አንተነህ የዋህ መልአክት የእርግብ አምሳል
የብርሃን አክሊል ነህ ሚካኤል ኃያል

አዝ ============

ለኔ ያለህን ፍቅር በዓይኔ አይቻለሁ
ውለታህን ሳስብ እጅግ አደንቃለሁ
በነፍስም በስጋም መታመኛዬ
የምትጥብቀኝ መከታ ጋሻዬ

አዝ ===========

ስወጣ ስገባ ከሌሎች እንቅፋት
ሚካኤል ጠብቀኝ ከሚገጥመኝ ጥፋት
ደግ ነው ሚካኤል ፍቅሩ በዝቶልኛል
በዘመኔ ሁሉ እሱ ይረዳኛል

 ★ ለሁሉም የተዋሃዶ ልጅች እንዲዳረስ #ሼር #ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ይቀላቀሉን★

╭══ ❀:✧๑♡๑✧❀ ══╮
@kedusangdamat
╰══ೋ•✧๑♡๑✧ ══╯
214 viewsEskedar Zeleka, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:06:59
163 viewsEskedar Zeleka, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:06:59
158 viewsEskedar Zeleka, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:06:59#ሰኔ_12 በዚህች ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ከሰይጣን እጅ ያዳነበት ቀን ነው ።
ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን ጻድቁ ንጉስ ቅዱስ ላሊበላ ያረፈበት ቀን ነው ።
➽ ቅድስት አፎምያ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር፤ በዚህ ሰይጣን ቀናባት በመነኩሴ ተመስሎ ሊያስታት ሞከረ በቅዱስ ሚካኤል ስዕል አሳፍራ መለሰችው ከ 3 ወራት በኃላ ሰኔ 12 ቀን ዳግመኛ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ ሊፈትናት መጣ፤ ሚካኤል ከሆንክ መስቀልህ የት አለ አለችው ከዚህ በኃላ አፉን ከፍቶ አይኑን አጉረጥርጦ አንገቷን አነቃት “ቅዱስ ሚካኤል ድረስልኝ” ብላ ተጣራች ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወረደ በበትረ መስቀሉም መታው ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ ስዕልህ ባለበት፤ ስምህ በተጠራበት፤ ድርሳንህ በሚነበብበት፤ ፈጽሞ አልደርስም ብሎ ማለ፤ ተገዘተ ሸሸም፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎምያን “ወዳጄ አፎምያ ባነቺ ደስ አለኝ ወጋሽ በሰማይ ታላቅ ነው” ብሎ ባርኳት አርጓል።
➽ ቅዱስ ላሊበላ (ላልይበላል) ላል ማለት ማር ማለት ነው፤ሲወለድ በንብ ተከቦ ነበርና ማር ይበላል “ላልይበላል” አሉት ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ትባላች እረፍቷ ሐምሌ 27 ነው ልጁ ይትባረክ እረፍቱ መስከረም 24 ቀን ነው ቅዱስ ላሊበላ 40 ዓመት ኢትዮጰያን አስተዳደረ ዓለምን የሚያስደንቅ እጹብ እጽብ የሚያሰኝ ከአንድ አለት ብቻ እጀታ በሌለው መጥረቢያ 12 ውቅር አብያተክርስቲያናትን አነጸ፤ እነዚህ በአንድ ቦታ ስላሉ ነው እንጂ በወሎ በጎንደር በሸዋ ለቁጥር የሚበዙ አብያተክርስቲያናትን አንጿል፤ ታህሳስ 29 ቀን ተወልዶ በ 80 ዓመቱ ሰኔ 12 በዛሬዋ ቀን አርፏል። መጨረሻ ያነጸው ቤተክርስቲያን አዳዲ ማርያምን ነው፤ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ናቸው እንዲያንጽ የጠየቁት እርሱም ጀምሮ ሳይጨርስ አቡነገብረመንፈስ ቅዱስ ወደርሱ ቀርበው ወዳጄ ላሊበላ የእረፍትህ ቀን ደርሷልና ወደ ላስታ ተመለስ አሉት እርሱም ተመለሰ በዚያም አረፈ፤ እራሱ ባነጸው በቤተ ጎሎጎታ ተቀበረ በመቃብሩም ላይ ለ 10 ቀን የማይጠፋ ብርሃን ሲበራ ይታይ ነበር። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

★ ለሁሉም የተዋሃዶ ልጅች እንዲዳረስ #ሼር #ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ይቀላቀሉን★

╭══ ❀:✧๑♡๑✧❀ ══╮
@kedusangdamat
╰══ೋ•✧๑♡๑✧ ══╯
166 viewsEskedar Zeleka, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 11:37:04
★ ለሁሉም የተዋሃዶ ልጅች እንዲዳረስ #ሼር #ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ይቀላቀሉን ★
╭══ ❀:✧๑♡๑✧❀ ══╮
@kedusangdamat
╰══ೋ•✧๑♡๑✧ ══╯
283 viewsZeleke eskey, 08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 11:35:33 ➻ አባቶቻችን በአባቶቻቸው እግር ተንበርክከው አላፊነትን ሲቀበሉ የሚያሳይ ፎቶ

➻ ብጹዓን አባቶቻችን በአባቶቻቸው እግር ስር እንዲህ ተንበርክከው ማየት እራሱ በቂ ትምህርት ነው

➻ ኦ አበዊነ ንቡራነ እድ ሥዩማን እለ መትልወ ሐዋርያት እስመ ነሣዕናክሙ አስተብቋዕያነ ለነ ለሀበ እግዚአብሔር

➻ ከሐዋርያት ቀጥላችሁ ሐዋርያትን መስላችሁ በአንብሮተ እድ የምትሾሙ አባቶቻችን ወደ እግዚአብሔር ልታቀርቡን ከእግዚአብሔር አግኝተን ተቀብለናችኋልና

ናፈቅረከሙ ወነዐብየክሙ

➻ እንወዳችኋለን እናከብራችኋለን እናገናችኋለን መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላችሁ።
✞ በረከታችሁ በሁላችንም ትደርብን። ★ ለሁሉም የተዋሃዶ ልጅች እንዲዳረስ #ሼር #ጆይን በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ይቀላቀሉን ★
╭══ ❀:✧๑♡๑✧❀ ══╮
@kedusangdamat
╰══ೋ•✧๑♡๑✧ ══╯
240 viewsZeleke eskey, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:10:17

240 viewsEskedar Zeleka, 03:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 05:03:44
217 viewsEskedar Zeleka, 02:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 00:53:22
" ማርያም ሆይ ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ "
••
#መልክአ_ማርያም
••
ለሌሎች ሼር በማድረግ ይጋብዙ
••••
https://t.me/kedusangdamat
https://t.me/kedusangdamat
579 viewsEskedar Zeleka, 21:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ